ኢሳይያስ 36:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በሕይወት ልትኖሩ ብትወድዱ ሁላችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ትጠጣላችሁ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “ሕዝቅያስን አትስሙ። የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእኔ ጋራ ተስማሙ፤ ወደ እኔም ውጡ። ከዚያም እያንዳንዳችሁ ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ሕዝቅያስን አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ኑ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጉድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ! የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፦ ወደ እኔ ኑና ከእኔ ጋር ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላ የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሕዝቅያስንም አትስሙ፥ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ፥ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፥ 参见章节 |