ኢሳይያስ 36:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ኤልያቄምና ሳምናስ፥ ዮአስም ራፋስቂስን፥ “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕብራይስጥ አትናገረን” አሉት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ኤልያቄም፣ ሳምናስና ዮአስ የጦር አዛዡን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ስለምንሰማ፣ እባክህን በሶርያ ቋንቋ ተናገር፤ በቅጥሩ ላይ ያሉት ሰዎች በሚሰሙት በዕብራይስጥ አትናገረን” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከዚያም ኤልያቄም፥ ሳምናስና ዮአስ ራፋስቂስን፦ “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሚገባን በሶርያ ቋንቋ ለአገልጋዮችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ መግባቢያ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን” አሉት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ከዚህ በኋላ ኤልያቄም፥ ሼብናና ዮአሕ የአሦራውያኑን ባለ ሥልጣን “እኛ ትርጒሙን ስለምናውቅ በሶርያ ቋንቋ እንድትነግረን እንለምንሃለን፤ በቅጽር ላይ ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሚሰሙት በዕብራይስጥ ቋንቋ አትንገረን” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ኤልያቄምና ሳምናስ ዮአስም ራፋስቂስን፦ እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባርያዎችህ ተናገር፥ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን አሉት። 参见章节 |