Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 36:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እና​ጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ወደ​ዚህ ሀገር ዘም​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ሀገ​ራ​ቸው ዘም​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው” አለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደግሞስ ይህን ምድር ለማጥቃትና ለማጥፋት የመጣሁት ያለ እግዚአብሔር ይመስልሃልን? በዚህች አገር ላይ ዘምቼ እንዳጠፋት የነገረኝ ራሱ እግዚአብሔር ነው።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሁንም ቢሆን፥ ጌታ፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ እንጂ፥ በውኑ ያለ ጌታ ይህን አገር ለማጥፋት የዘመትኩ ይመስልሃል?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔስ ብሆን ይህንን አገር ለመውረርና ለማጥፋት የቻልኩት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እንዲያውም በአገሪቱ ላይ አደጋ ጥዬ እንዳጠፋት ያዘዘኝ እግዚአብሔር ራሱ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ይህን አገር አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 36:10
8 交叉引用  

እር​ሱም፥ “እኔ ደግሞ እን​ዳ​ንተ ነቢይ ነኝ፤ መል​አ​ክም፦ እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ወደ ቤትህ መል​ሰው ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ተና​ገ​ረኝ” አለው። ዋሽ​ቶም ተና​ገ​ረው።


ነቢ​ያ​ትም ሁሉ እን​ዲህ ብለው ትን​ቢት ተና​ገሩ፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ዝመት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይረ​ዳ​ሃል። ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ነቢ​ያ​ቱን አራት መቶ የሚ​ያ​ህ​ሉ​ትን ሰዎች ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ውጣ” አሉት።


አሁን በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይህን ስፍራ እና​ጠፋ ዘንድ ወጥ​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ​ዚች ሀገር ወጥ​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አት አለን።”


እር​ሱም፥ “የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? በም​ዋ​ጋ​በት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአ​ንተ ላይ ዛሬ አል​መ​ጣ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ድ​ቸ​ኩል አዝ​ዞ​ኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ​በት።


አሁን ግን እኔ መቀ​መ​ጫ​ህ​ንና መው​ጫ​ህን፥ መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ።


ወይስ በከ​ተማ ውስጥ መለ​ከት ሲነፋ ሕዝቡ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ክፉ ነገር በከ​ተማ ላይ ይመ​ጣ​ልን?


跟着我们:

广告


广告