ኢሳይያስ 34:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ጢሱም ወደላይ ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለብዙ ዘመናትም ትጠፋለች። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እሳቷ ሌሊትና ቀን አይጠፋም፤ ጢሷም ለዘላለም ይትጐለጐላል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድ ባድማ ትሆናለች፤ ማንም በዚያ ዳግም አያልፍም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 በሌሊትና በቀንም አትጠፋም፤ ጢስዋም ለዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘለዓለም ዓለም ማንም አያልፍባትም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ቀንና ሌሊት ትቃጠላለች፤ ጢስም ከእርስዋ መውጣቱን ለዘለዓለም አያቋርጥም፤ ምድሪቱም በዘመናት ሁሉ የማትጠቅም ባድማ ትሆናለች፤ ዳግመኛ በእርስዋ ውስጥ አልፎ የሚሄድ አይኖርም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 በሌሊትና በቀንም አትጠፋም፥ ጢስዋም ለዘላለም ይወጣል፥ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፥ ለዘላለም ዓለም ማንም አያልፍባትም። 参见章节 |