ኢሳይያስ 30:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ ቍጣውም ከከንፈሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነድዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተመላ ነው፤ የቍጣውም መቅሠፍት እንደምትበላ እሳት ናት፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 እነሆ፤ የእግዚአብሔር ስም፣ ከሚነድድ ቍጣ፣ ጥቅጥቅ ካለና ከሚትጐለጐል የጢስ ደመና ጋራ ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹ ቍጣን የተሞሉ ናቸው፤ ምላሱም የሚባላ እሳት ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 እነሆ፥ የጌታ ስም ከሚነድ ቁጣ፥ ከሚንቦለቦልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹም በቁጣ የተሞሉ ናቸው፥ ምላሱም እንደምትበላ እሳት ናት፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እነሆ፥ የእግዚአብሔር ኀይልና ግርማ ከሩቅ ይታያል፤ ነበልባልና ጢስ የቊጣው ምልክቶች ናቸው፤ በሚናገርበትም ጊዜ ቃሉ እንደ እሳት ይነዳል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከሚነድድ ቍጣ ከሚትጐለጐልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፥ ከንፈሮቹም ቍጣን የሞሉ ናቸው፥ ምላሱም እንደምትበላ እሳት ናት፥ 参见章节 |