Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ብት​ጸ​ጸ​ትና ብታ​ለ​ቅስ ትድ​ና​ለህ፤ የት እን​ዳ​ለ​ህም ታው​ቃ​ለህ፤ በከ​ንቱ ታም​ነ​ሃ​ልና፤ ኀይ​ላ​ች​ሁም ከንቱ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አላ​ችሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ትበረታላችሁ፤ እናንተ ግን ይህን አላደረጋችሁም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ ኃይላችሁ በጸጥታና በመታመን ይሆናል፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመመለስና በማረፍ ደኅንነትን ታገኛላችሁ፤ ጸጥ በማለትና በመታመን ኀይል ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፥ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፥ እናንተም እምቢ አላችሁ፥

参见章节 复制




ኢሳይያስ 30:15
26 交叉引用  

በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።


ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንና የል​ብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች የነ​በ​ሩ​አ​ቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አል​ነ​በ​ሩ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታመ​ንህ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


ከእ​ርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚ​ረ​ዳን የሚ​ዋ​ጋ​ል​ንም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።” ሕዝ​ቡም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ቃል ተጽ​ናና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋል፤ እና​ን​ተም ዝም ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።


እር​ሱም፥ “ይህ​ችም ለደ​ከመ ዕረ​ፍት ናት፤ ይህ​ችም መቅ​ሠ​ፍት ናት፤” አላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አሉ።


“ከዚህ መን​ገድ መል​ሱን፤ ከዚ​ህም ፈቀቅ አድ​ር​ጉን በሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ ትም​ህ​ርት ከእኛ ዘንድ አስ​ወ​ግዱ” ይሏ​ቸ​ዋል።


የግ​ብፅ ርዳታ ከን​ቱና ባዶ ነው፤ ስለ​ዚህ፥ “ምክ​ራ​ችሁ ከንቱ ነው” ብለህ ንገ​ራ​ቸው።


የጽ​ድ​ቅም ሥራ ሰላም ይሆ​ናል፤ ጽድ​ቅም የዕ​ረ​ፍት ቦታን ይይ​ዛል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይታ​መ​ኑ​በ​ታል።


ሕዝ​ቤም በሰ​ላም ከተማ ይኖ​ራል። ተዘ​ል​ሎም በው​ስ​ጥዋ ያድ​ራል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ናም ያር​ፋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


ያዕ​ቆ​ብን እን​ዲ​ማ​ር​ኩት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም እን​ዲ​በ​ዘ​ብ​ዙት ያደ​ረገ ማን ነው? እነ​ር​ሱም የበ​ደ​ሉት፥ በመ​ን​ገ​ዱም ይሄዱ ዘንድ ያል​ወ​ደ​ዱት፥ ሕጉ​ንም ያል​ሰ​ሙት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?


እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ።


እን​ዲ​ህም በለው፥ “ተጠ​በቅ፥ ዝምም በል፤ አት​ፍራ፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሚ​ጤሱ ሁለት የእ​ን​ጨት ጠለ​ሸ​ቶች፥ የተ​ነሣ ልብህ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ ከተ​ቈ​ጣሁ በኋላ ይቅር እላ​ለ​ሁና።


ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆ​ን​በ​ታ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ብላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ጥሩ፤ የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ያ​ውን አም​ላክ ቃል ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና።


የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ፤ ሊመጡም አልወደዱም።


“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።


“ነቢ​ያ​ትን የም​ት​ገ​ድ​ሊ​ያ​ቸው፥ ወደ አንቺ የተ​ላ​ኩ​ትን ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም የም​ት​ደ​በ​ድ​ቢ​ያ​ቸው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዶሮ ጫጩ​ቶ​ች​ዋን ከክ​ን​ፍዋ በታች እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ ልጆ​ች​ሽን ልሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ምን ያህል ወደ​ድሁ? ነገር ግን እንቢ አላ​ችሁ።


ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ወደ እኔ ልት​መጡ አት​ወ​ዱም።


ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ?


跟着我们:

广告


广告