Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 30:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ነቢ​ያ​ትን፥ “አት​ን​ገ​ሩን፤ ባለ ራእ​ዮ​ች​ንም አታ​ው​ሩን፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ስሕ​ተት አስ​ረ​ዱን፤ ንገ​ሩ​ንም” ይላሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ባለራእዮችን፣ “ከእንግዲህ ራእይን አትዩ!” ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤ “እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ ደስ የሚያሠኘውን ንገሩን፤ የሚያማልለውን ተንብዩልን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ባለ ራእዮችን፦ “አትመልከቱ” ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ “ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ባለ ራእዮችን፦ አትመልከቱ ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፥

参见章节 复制




ኢሳይያስ 30:10
39 交叉引用  

ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ በፊቱ የነ​በ​ረ​ውን ሰው ገደለ፤ ደጋ​ግ​መ​ውም ገደሉ። ከዚ​ህም በኋላ ሶር​ያ​ው​ያን ሸሹ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴ​ርም በፈ​ጣን ፈረስ አመ​ለጠ።


ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት በሉ​አ​ቸው” አለ።


አሳም በነ​ቢዩ በአ​ናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና በግ​ዞት አኖ​ረው፤ በዚ​ያን ጊዜም አሳ ከሕ​ዝቡ አያሌ ሰዎ​ችን አስ​ጨ​ነቀ።


እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ንጉሡ አሜ​ስ​ያስ፥ “በውኑ የን​ጉሡ አማ​ካሪ ልት​ሆን ሹሜ​ሃ​ለ​ሁን? ቅጣት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። ነቢ​ዩም፥ “ይህን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ምክ​ሬ​ንም አል​ሰ​ማ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋህ እን​ዳ​ሰበ አወ​ቅሁ” ብሎ ዝም አለ።


ስለ እርሱ ዝም አል​ልም፥ የኀ​ይል ቃልም እንደ እርሱ ያለ​ውን ይቅር ይለ​ዋል።


እና​ን​ተም “ከሲ​ኦል ጋር ተማ​ም​ለ​ናል፤ ከሞ​ትም ጋር ቃል ኪዳን አድ​ር​ገ​ናል፤ ሐሰ​ት​ንም መሸ​ሸ​ጊ​ያን አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ተሰ​ው​ረ​ና​ልና፥ ዐውሎ ነፋ​ስም ባለፈ ጊዜ አይ​ደ​ር​ስ​ብ​ንም” ትላ​ላ​ች​ሁና፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ን​ቅ​ልፍ መን​ፈ​ስን አፍ​ስ​ሶ​ባ​ቸ​ዋል፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን፥ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ዐይን፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያዩ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን ዐይን ጨፍ​ኖ​ባ​ቸ​ዋል።


ክፉ​ውን መል​ካም መል​ካ​ሙ​ንም ክፉ ለሚሉ፥ ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን ብር​ሃ​ኑ​ንም ጨለማ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ ጣፋ​ጩን መራራ መራ​ራ​ው​ንም ጣፋጭ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ወዮ​ላ​ቸው!


ስለ​ዚ​ህም፥ “በእ​ጃ​ችን እን​ዳ​ት​ሞት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ትን​ቢት አት​ና​ገር” ብለው ነፍ​ሴን ስለ​ሚሹ ስለ አና​ቶት ሰዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ።


ካህ​ና​ቱና ነቢ​ያተ ሐሰ​ትም ለአ​ለ​ቆ​ቹና ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “በጆ​ሮ​አ​ችሁ እንደ ሰማ​ችሁ በዚች ከተማ ላይ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ይህ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው” ብለው ተና​ገሩ።


አሁ​ንስ ትን​ቢት ተና​ጋ​ሪ​ውን የአ​ና​ቶ​ቱን ሰው ኤር​ም​ያ​ስን ስለ ምን አት​ዘ​ል​ፈ​ውም?


የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄ​ምን እን​ዲህ በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በር​ግጥ ይመ​ጣል፤ ይች​ንም ሀገር ያፈ​ር​ሳ​ታል፤ ሰውና እን​ስ​ሳም ያል​ቃሉ ብለህ ለምን ጻፍ​ህ​በት? ብለህ ይህን ክር​ታስ አቃ​ጥ​ለ​ሃል።


አለ​ቆ​ቹም ንጉ​ሡን፥ “ይህን የመ​ሰ​ለ​ውን ቃል ሲነ​ግ​ራ​ቸው በዚ​ያች ከተማ የቀ​ሩ​ትን የሰ​ል​ፈ​ኞ​ቹን እጅ፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሁሉ እጅ ያደ​ክ​ማ​ልና ይህ ሰው ይገ​ደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋ​ትን እንጂ ሰላ​ምን አይ​መ​ኝ​ለ​ት​ምና” አሉት።


ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


“እና​ንተ ግን ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን የወ​ይን ጠጅ አጠ​ጣ​ች​ኋ​ቸው፤ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ “ትን​ቢ​ትን አት​ና​ገሩ ብላ​ችሁ ከለ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸው።


ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።


ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።


ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።


ዓለም እና​ን​ተን ሊጠ​ላ​ችሁ አይ​ች​ልም፤ እኔን ግን ይጠ​ላ​ኛል፤ ሥራዉ ክፉ እንደ ሆነ እኔ እመ​ሰ​ክ​ር​በ​ታ​ለ​ሁና።


እኔ ግን እው​ነ​ትን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና አታ​ም​ኑ​ኝም።


ነገር ግን በሕ​ዝቡ ዘንድ እጅግ እን​ዳ​ይ​ስ​ፋፋ ዳግ​መኛ በኢ​የ​ሱስ ስም ሰውን እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ አጠ​ን​ክ​ረን እን​ገ​ሥ​ጻ​ቸው።”


“በኢ​የ​ሱስ ስም ለማ​ንም እን​ዳ​ታ​ስ​ተ​ምሩ ከል​ክ​ለ​ና​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እነሆ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በት​ም​ህ​ር​ታ​ችሁ ሞላ​ች​ኋት፤ የዚ​ያ​ንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመ​ጡ​ብን ዘንድ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


እው​ነ​ቱን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ባላ​ጋራ ሆን​ኋ​ች​ሁን?


ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።


እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ።


ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል፤ ያሸንፋቸውማል፤ ይገድላቸውማል።


ቀድሞ ነቢ​ዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበ​ርና አስ​ቀ​ድሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እን​ሂድ ይል ነበር።”


跟着我们:

广告


广告