Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 3:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የም​ት​ወ​ጂው ትልቁ ልጅሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ኀያ​ላ​ን​ሽም በው​ጊያ ይወ​ድ​ቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ወንዶቻችሁ በሰይፍ ስለት፣ ተዋጊዎቻችሁ በጦርነት ይወድቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ወንዶቻችሁ በሰይፍ ስለት፤ ተዋጊዎቻችሁ በጦርነት ይወድቃሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ጐልማሶችሽ በሰይፍ፥ ኀያላንሽም በጦር ሜዳ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ጕልማሶችሽ በሰይፍ፥ ኃያላንሽም በውጊያ ይወድቃሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 3:25
12 交叉引用  

የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በአ​ንድ ቀን ከይ​ሁዳ ጽኑ​ዓን የነ​በሩ መቶ ሃያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞ​ችን ገደለ፤


እነ​ሆም፥ ስለ​ዚህ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ይፍ ወደቁ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የእ​ነ​ርሱ ሀገር ወዳ​ል​ሆነ ተማ​ረኩ፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖ​ራሉ።


እንቢ ብት​ሉና ባት​ሰ​ሙኝ ግን ሰይፍ ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


እኔም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሁላ​ች​ሁም በሰ​ይፍ ትገ​ደ​ላ​ላ​ችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረ​ጣ​ችሁ እንጂ በጠ​ራ​ኋ​ችሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝ​ምና።”


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ቸው በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በራብ ይሞ​ታሉ፤


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰ​ይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተ​ማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢ​ዩና ካህኑ ወደ​ማ​ያ​ው​ቋት ሀገር ሄደ​ዋ​ልና።”


መበ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ በዝ​ተ​ዋል፤ በብ​ላ​ቴ​ኖች እናት ላይ በቀ​ትር ጊዜ አጥ​ፊ​ውን አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ ጭን​ቀ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን በድ​ን​ገት አም​ጥ​ቼ​ባ​ታ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


በዚ​ህም ስፍራ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ምክር አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት በጦ​ርና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን በሚ​ሹት እጅ እጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ቸ​ው​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ለሁ።


በዚ​ህች ከተማ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወጥቶ ወደ ከበ​ቡ​አ​ችሁ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ገባ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሰው​ነ​ቱም ምርኮ ትሆ​ና​ለች።


ሣን። ብላ​ቴ​ና​ውና ሽማ​ግ​ሌው በመ​ን​ገ​ዶች ላይ ተጋ​ደሙ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ወድ​ቀ​ዋል፤ በረ​ኃብ ገደ​ል​ሃ​ቸው፤ በቍ​ጣ​ህም ቀን ሳት​ራራ አረ​ድ​ሃ​ቸው።


ክፉው ነገር አይ​ደ​ር​ስ​ብ​ንም፤ አያ​ገ​ኘ​ን​ምም የሚሉ የሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሁሉ በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ።


跟着我们:

广告


广告