Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የከ​በ​ሮ​አ​ቸው ደስታ አል​ቆ​አል፤ መታ​ጀ​ራ​ቸ​ውም አል​ቃ​ለች፤ የኃ​ጥ​ኣን ሀብት አል​ቆ​አል፤ የመ​ሰ​ንቆ ድም​ፅም ቀር​ቶ​አል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የከበሮ ደስታ ጸጥ አለ፤ የጨፋሪዎች ጩኸት አበቃ፤ ደስ የሚያሠኘውም በገና እረጭ አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የከበሮው ሐሤት ቀርቷል፥ የደስተኞች ድምጽ ዝም ብሏል፥ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሚያስደስት የመሰንቆ፥ ሙዚቃና የአታሞ ድምፅ መሰማቱ ቀርቶአል፤ የበዓል አከባበር ሁሉ ቆሞአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የከበሮው ሐሤት ቀርቷል፥ የደስተኞች ድምጽ ዝም ብሏል፥ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 24:8
16 交叉引用  

ለዚ​ያም ሌሊት ጭንቅ ይሁን፥ እል​ልታ ወይም ደስታ አይ​ግ​ባ​ባት።


ስለ​ዚህ ሕማሜ መሰ​ንቆ፥ ልቅ​ሶ​ዬም በገና ሆነ​ብኝ።


በቤተ መቅ​ደ​ስ​ህም እሰ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ስም​ህን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስም​ህን ከፍ ከፍ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና።


ደስ​ታና ሐሤ​ትም ከወ​ይን ቦታሽ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ በወ​ይ​ን​ሽም ቦታ​ዎች ፈጽ​መው ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም፤ በመ​ጥ​መ​ቂ​ያ​ውም ወይ​ንን አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ረጋ​ጮ​ቹን አጥ​ፍ​ቻ​ለ​ሁና።


በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በከ​በ​ሮና በእ​ም​ቢ​ል​ታም እየ​ዘ​ፈኑ የወ​ይን ጠጅን ይጠ​ጣሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ቱም፤ የእ​ጁ​ንም ሥራ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


ሲኦ​ልም ሆድ​ዋን አስ​ፍ​ታ​ለች፤ አፍ​ዋ​ንም ያለ ልክ ከፍ​ታ​ለች፤ የተ​ከ​በ​ሩና ታላ​ላቅ ሰዎች ባለ​ጠ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ድሆ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እር​ስዋ ይወ​ር​ዳሉ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በዘ​መ​ና​ች​ሁም የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


ከእ​ነ​ር​ሱም የሐ​ሤ​ትን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ጽና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ፥ የወ​ፍ​ጮ​ንም ድምፅ የመ​ብ​ራ​ት​ንም ብር​ሃን አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


ምድ​ሪ​ቱም ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ አጠ​ፋ​ለሁ።


ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ደ​ባ​ባይ ጠፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ችም ከበ​ገ​ና​ቸው ተሻሩ።


የዘ​ፋ​ኞ​ች​ሽ​ንም ብዛት ዝም አሰ​ኛ​ለሁ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ሽም ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይ​ሰ​ማም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት በዔ​ድን ነበ​ርህ፤ የከ​በረ ዕን​ቍስ ሁሉ፥ ሰር​ድ​ዮን፥ ቶጳ​ዝ​ዮን፥ አል​ማዝ፥ ቢረሌ፥ መረ​ግድ፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፥ ሰን​ፔር፥ በሉር፥ የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ፥ ወር​ቅም ልብ​ስህ ነበረ፤ የከ​በ​ሮ​ህና የእ​ን​ቢ​ል​ታህ ሥራ በአ​ንተ ዘንድ ነበረ፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በ​ትም ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ነበር።


ደስ​ታ​ዋ​ንም ሁሉ፥ በዓ​ላ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ መባ​ቻ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ሰን​በ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው አስ​ቀ​ድ​መው ይማ​ረ​ካሉ፤ ሯጮች የሚ​ሆኑ የኤ​ፍ​ሬም ፈረ​ሶ​ችም ያል​ቃሉ።


በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤


跟着我们:

广告


广告