Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 24:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በባ​ሕር ደሴ​ቶች ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ይከ​ብ​ራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ በምሥራቅ ለእግዚአብሔር ክብር ስጡ፤ ከባሕር ደሴቶችም፣ የእስራኤልን አምላክ፣ የእግዚአብሔርን ስም ከፍ ከፍ አድርጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህ ጌታን በምሥራቅ፥ የእስራኤልንም አምላክ የጌታንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ በምሥራቅ ያሉት ለእግዚአብሔር ክብር ይሰጣሉ፤ በደሴቶች ያሉ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስለዚህ እግዚአብሔርን በምሥራቅ፥ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 24:15
26 交叉引用  

በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ስሙ​ንም ጥሩ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ክብ​ሩን አስ​ታ​ውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስ​ታ​ውሱ።


ስለ​ዚህ ድሆች ወገ​ኖች ያከ​ብ​ሩ​ሃል፤ የተ​ገፉ ሰዎች ከተ​ሞ​ችም ያከ​ብ​ሩ​ሃል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና ነው፤ በቅ​ዱስ ስሙም ታመን፤ ነፍ​ሳ​ችን የተ​መ​ኘ​ች​ው​ንም አገ​ኘን።


አሕ​ዛብ አይ​ተው ፈሩ። የም​ድ​ርም ዳር​ቾች ቀረቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ቀረቡ፤ መጡም።


ወደ ባሕር የም​ት​ወ​ርዱ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ የም​ት​ጓዙ ሁሉ፥ ደሴ​ቶ​ችና በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ መዝ​ሙር ዘምሩ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ስሙን አክ​ብሩ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ይስጡ፤ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በደ​ሴ​ቶች ይና​ገሩ።


በም​ድ​ርም ፍር​ድን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ያበ​ራል እንጂ አይ​ጠ​ፋም፤ አሕ​ዛ​ብም በስሙ ይታ​መ​ናሉ።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤


ጽድቄ ፈጥና ትመ​ጣ​ለች፤ ማዳ​ኔም እንደ ብር​ሃን ትደ​ር​ሳ​ለች፤ አሕ​ዛብ በክ​ንዴ ይታ​መ​ናሉ፤ ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ በክ​ን​ዴም ይታ​መ​ናሉ።


ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ የተ​ር​ሴ​ስም መር​ከ​ቦች አስ​ቀ​ድ​መው ይመ​ጣሉ፤ ልጆ​ችሽ ስለ ከበ​ረው ስለ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወር​ቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ምል​ክት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከሞት የዳ​ኑ​ትን ዝና​ዬን ወዳ​ል​ሰሙ፥ ክብ​ሬ​ንም ወዳ​ላዩ ወደ አሕ​ዛብ ወደ ተር​ሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴ​ቶች እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ክብ​ሬን ይና​ገ​ራሉ።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ጳው​ሎ​ስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በዜማ አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እስ​ረ​ኞ​ቹም ይሰ​ሙ​አ​ቸው ነበር።


ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።


跟着我们:

广告


广告