Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 24:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነ​ዚህ ድም​ፃ​ቸ​ውን ያነ​ሣሉ፤ በም​ድር የቀ​ሩ​ትም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የባ​ሕ​ርም ውኃ ይና​ወ​ጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ፤ በደስታም ይጮኻሉ፤ ከምዕራብም የእግዚአብሔርን ክብር ያስተጋባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እነዚህ ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ እልልም ይላሉ፥ ስለ ጌታ ክብርም ከባሕር ይጣራሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከጥፋት የተረፉት በደስታ እልል ይላሉ፤ በስተ ምዕራብ ያሉትም ሁሉ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ይናገራሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነዚህ ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ እልልም ይላሉ፥ ስለ እግዚአብሔር ክብርም ከባሕር ይጣራሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 24:14
20 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ፥ ድንቅ ነገ​ርን የዱሮ እው​ነ​ተኛ ምክ​ርን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።


በዚ​ያም ቀን ይህን ቅኔ በይ​ሁዳ ምድር ይዘ​ም​ራሉ፤ እነ​ሆም፥ የጸ​ና​ችና የም​ታ​ድን፥ ቅጥ​ር​ንና ምሽ​ግ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ከተማ አለ​ችን።


በዚ​ያም ቀን ለተ​ወ​ደ​ደው የወ​ይን ቦታ ተቀ​ኙ​ለት።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።


የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ምድረ በዳ ያብ​ባል፤ ሐሤ​ት​ንም ያደ​ር​ጋል፤ የሊ​ባ​ኖስ ክብ​ርና የቀ​ር​ሜ​ሎስ ክብር ይሰ​ጠ​ዋል፤ ሕዝ​ቤም የጌ​ታን ክብር፥ የአ​ም​ላ​ክ​ንም ግርማ ያያሉ።


ለጽ​ዮን የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ከፍ ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ድም​ፅ​ህን በኀ​ይል አንሣ፤ አት​ፍራ፤ ለይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ! ብለህ ንገር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።


ከባ​ቢ​ሎን ውጡ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ኰብ​ልሉ፤ በእ​ል​ልታ ድምፅ ተና​ገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድ​ርም ዳርቻ ድረስ አው​ሩና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ያ​ውን ያዕ​ቆ​ብን ታድ​ጎ​ታል” በሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቤ​ዣ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ወደ ጽዮ​ንም በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ክብር በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ደስ​ታ​ንና ተድ​ላን ያገ​ኛሉ፤ ኀዘ​ንና ልቅ​ሶም ይወ​ገ​ዳሉ።


አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዚያ ጊዜ አይ​ተሽ ትፈ​ሪ​ያ​ለሽ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብና የሀ​ገ​ሮች ብል​ጽ​ግና ወደ አንቺ ይመ​ለ​ሳ​ልና፥ ልብሽ ይደ​ነ​ግ​ጣል።


ከእ​ር​ሱም ዘንድ የም​ስ​ጋ​ናና የዘ​ፈን ድምፅ ይወ​ጣል፤ እኔም አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አያ​ን​ሱ​ምም።


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


የሐ​ሤት ድም​ፅና የደ​ስታ ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽራ ድም​ፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​መጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰ​ማል። የዚ​ያ​ችን ምድር ምር​ኮ​ኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ዳ​ች​ንን አው​ጥ​ቶ​አል፤ ኑ በጽ​ዮን የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ እን​ና​ገር።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ ደስም ይበልሽ፥ ይላል እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告