Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 22:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህ​ንም አለ​ብ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ አክ​ሊ​ል​ህ​ንም እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሹመ​ት​ህ​ንም በእጁ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ሩና በይ​ሁ​ዳም ለሚ​ኖሩ አባት ይሆ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 መጎናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፥ በመታጠቅያህም አስታጥቀዋለሁ፥ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የአንተ የነበረውን የማዕርግ ልብስ አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህንም እሰጠዋለሁ፤ የአንተ የነበረውንም ሥልጣን ሁሉ ለእርሱ አስረክባለሁ፤ እርሱ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሕዝቦች እንደ አባት ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 መጎናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፥ በመታጠቅያህም አስታጥቀዋለሁ፥ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 22:21
8 交叉引用  

አሁ​ንም እና​ንተ ወደ​ዚህ የላ​ካ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እንደ አባት አደ​ረ​ገኝ፤ በቤ​ቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ላይ አለቃ አደ​ረ​ገኝ።


ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።


በጥ​ቍር ቀለም የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን መልክ አየሁ፤ በወ​ገ​ባ​ቸው ዝናር የታ​ጠቁ ናቸው፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ጥልፍ ሰበን የጠ​መ​ጠሙ ናቸው፤ ፊታ​ቸ​ውም ሦስት ወገን ነው፤ ሁሉም በት​ው​ልድ ሀገ​ራ​ቸው የሚ​ኖሩ የባ​ቢ​ሎን ሰዎ​ችን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ይመ​ስ​ላሉ።


ዮና​ታ​ንም የለ​በ​ሰ​ውን ካባ አው​ልቆ እር​ሱ​ንና ልብ​ሱን፥ ሰይ​ፉ​ንም፥ ቀስ​ቱ​ንም፥ ዝና​ሩ​ንም ለዳ​ዊት ሸለ​መው።


跟着我们:

广告


广告