Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 19:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች አለቁ፤ የሜ​ም​ፎ​ስም አለ​ቆች ከፍ ከፍ አሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ተሳ​ሳቱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፊስ ሹማምት ተታልለዋል፤ የሕዝቧ ዋና ዋናዎች፣ ግብጽን አስተዋታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፎስም አለቆች ተታለዋል፤ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑት ግብጽን አስተዋታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የጾዓን ባለ ሥልጣኖች ሞኞች ሆኑ፤ የሜምፊስ መሪዎችም ተታለሉ፤ የሕዝብዋ ከፍተኛ አማካሪዎች ግብጽን አሳትዋት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል፥ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑ ግብጽን አሳቱ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 19:13
14 交叉引用  

የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች ሰነ​ፎች ይሆ​ናሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን የሚ​መ​ክሩ ጥበ​በ​ኞ​ችም ምክ​ራ​ቸው ስን​ፍና ትሆ​ና​ለች። ንጉ​ሥን፥ “እኛ የጥ​በ​በ​ኞች ልጆች፥ የቀ​ደሙ ነገ​ሥ​ታ​ትም ልጆች ነን እን​ዴት ትሉ​ታ​ላ​ችሁ?”


የሜ​ም​ፎ​ስና የጣ​ፍ​ናስ ልጆች አስ​ነ​ወ​ሩሽ፤ አላ​ገ​ጡ​ብ​ሽም።


በግ​ብፅ ምድር በሚ​ግ​ዶ​ልና በጣ​ፍ​ናስ፥ በሜ​ም​ፎ​ስም፥ በፋ​ቱ​ራም ሀገር ስለ ተቀ​መጡ አይ​ሁድ ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦


“በግ​ብፅ ተና​ገሩ፤ በሚ​ግ​ዶ​ልም አውሩ፤ በሜ​ም​ፎ​ስና በጣ​ፍ​ናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙ​ሪ​ያህ ያለ​ውን በል​ቶ​አ​ልና፦ ተነሥ ተዘ​ጋ​ጅም በሉ።


አንቺ በግ​ብፅ የም​ት​ቀ​መጪ ልጅ ሆይ! ሜም​ፎስ ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝ​ምና ለፍ​ል​ሰት የሚ​ሆን ዕቃ አዘ​ጋጂ።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣዖ​ቶ​ቹን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም ከሜ​ም​ፎስ እሽ​ራ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ያም በግ​ብፅ ምድር አለቃ አይ​ሆ​ንም፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ፍር​ሀ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ጳት​ሮ​ስ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በጣ​ኔ​ዎ​ስም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዲ​ዮ​ስ​ጶ​ሊን ላይም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


በግ​ብ​ፅም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ሲንም ትታ​ወ​ካ​ለች፤ ኖእም ትሰ​በ​ራ​ለች፤ ሜም​ፎ​ስም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች።


ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል።


ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፍ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ።


አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።


ጥበ​በ​ኞች ነን ሲሉ አላ​ዋ​ቆች ሆኑ።


እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን “አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ


ሳኦ​ልም፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ችን ሁሉ ወደ​ዚህ አቅ​ርቡ፤ ዛሬ ይህ ኀጢ​ኣት በማን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤


跟着我们:

广告


广告