Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች ሰነ​ፎች ይሆ​ናሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን የሚ​መ​ክሩ ጥበ​በ​ኞ​ችም ምክ​ራ​ቸው ስን​ፍና ትሆ​ና​ለች። ንጉ​ሥን፥ “እኛ የጥ​በ​በ​ኞች ልጆች፥ የቀ​ደሙ ነገ​ሥ​ታ​ትም ልጆች ነን እን​ዴት ትሉ​ታ​ላ​ችሁ?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የጣኔዎስ አለቆች በጣም ቂሎች ናቸው፤ የፈርዖን ጠቢባን ምክራቸው የማይረባ ነው፤ ፈርዖንን፣ “እኔ ከጥበበኞች አንዱ ነኝ፤ የጥንት ነገሥታትም ደቀ መዝሙር ነኝ” እንዴት ትሉታላችሁ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው እርባና ቢስ ይሆናል። ፈርዖንን “እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን” እንዴት ትሉታላችሁ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በጾዓን ያሉ የንጉሡ ባለ ሥልጣኖች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ጠቢባን የሆኑት የግብጽ ንጉሥ አማካሪዎች ጥቅም የሌለው ምክር ይመክራሉ፤ እንዴት አድርገው ለንጉሡ “እኛ ብልኆች ነን፤ ዘራችንም ከቀድሞ ነገሥታት ሲወርድ፥ ሲዋረድ የመጣ ነው” ይላሉ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፥ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው ድንቍርና ሆነች። ፈርዖንን እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?

参见章节 复制




ኢሳይያስ 19:11
31 交叉引用  

የሰ​ሎ​ሞ​ንም ጥበብ ከቀ​ደሙ ሰዎች ሁሉ ጥበ​ብና ከግ​ብፅ ጥበብ ሁሉ በዛ።


እን​ዲ​ሁም ኪራም የዝ​ግ​ባ​ው​ንና የጥ​ዱን እን​ጨት፥ የሚ​ሻ​ው​ንም ሁሉ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


መካ​ሮ​ች​ንም እን​ዲ​ማ​ረኩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ች​ንም አላ​ዋ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


ባለ​ጠ​ጎች ደኸዩ፥ ተራ​ቡም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ል​ጉት ግን ከመ​ል​ካም ነገር ሁሉ አል​ተ​ቸ​ገ​ሩም።


አቤቱ፥ ተነሥ፥ በቀ​ሌ​ንም ተበ​ቀል፤ ሰነ​ፎች ሁል​ጊዜ የተ​ገ​ዳ​ደ​ሩ​ህን ዐስብ።


አቤቱ፥ የተ​ገ​ዳ​ደ​ሩ​ህን መገ​ዳ​ደ​ራ​ቸ​ውን፥ ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን ሰባት እጥፍ በብ​ብ​ታ​ቸው ክፈ​ላ​ቸው።


እንደ ክም​ርም አድ​ር​ገው ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ምድ​ርም ገማች።


ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችም በአ​ንተ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ላይ ይወ​ጣሉ።”


የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች አለቁ፤ የሜ​ም​ፎ​ስም አለ​ቆች ከፍ ከፍ አሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ተሳ​ሳቱ።


የግ​ብ​ፅም መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ምክ​ራ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ይ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድ​ጋሚ እን​ዲ​ፈ​ልስ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ የጥ​በ​በ​ኞ​ች​ንም ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ተ​ዋ​ዮ​ች​ንም ማስ​ተ​ዋል እሰ​ው​ራ​ለሁ።”


አለ​ቆች ምንም በጣ​ኔ​ዎስ ቢሆኑ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ምንም ወደ ሓኔስ ቢደ​ርሱ፥


በሟ​ርት ሙት እና​ስ​ነ​ሣ​ለን የሚ​ሉ​ትን፥ ከል​ባ​ቸ​ውም አን​ቅ​ተው ሐሰት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሰዎች ምል​ክት የሚ​ለ​ውጥ ማን ነው? ጥበ​በ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ኋላ ይመ​ል​ሳል፤ ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ስን​ፍና ያደ​ር​ጋል።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል።


በዚ​ያም የግ​ብፅ ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ስም ጊዜ​ውን የሚ​ያ​ሳ​ልፍ ብለው ጠሩት።


ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?


ጥበ​በ​ኞች አፍ​ረ​ዋል፤ ደን​ግ​ጠ​ው​ማል፤ ተማ​ር​ከ​ው​ማል፤ እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጥለ​ዋል፤ ምን ዓይ​ነት ጥበብ አላ​ቸው?


በው​በ​ትህ ምክ​ን​ያት ልብህ ኰር​ቶ​አል፤ ከክ​ብ​ርህ የተ​ነሣ ጥበ​ብ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ በም​ድር ላይ ጣል​ሁህ፤ ያዩ​ህም፥ ይዘ​ብ​ቱ​ብ​ህም ዘንድ በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት አሳ​ልፌ ሰጠ​ሁህ።


ጳት​ሮ​ስ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በጣ​ኔ​ዎ​ስም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዲ​ዮ​ስ​ጶ​ሊን ላይም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ድን​ጋጤ በድ​ን​ጋጤ ላይ ይመ​ጣል፤ ወዮታ በወ​ዮታ ላይ ይከ​ተ​ላል፤ ከነ​ቢ​ዩም ዘንድ ራእ​ይን ይሻሉ፤ ከካ​ህ​ኑም ዘንድ ሕግ፥ ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ዘንድ ምክር ይጠ​ፋል።


የተ​ማ​ማ​ል​ሃ​ቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ዳር​ቻህ ሰደ​ዱህ፤ የተ​ስ​ማ​ሙ​ህም ሰዎች ተነ​ሡ​ብህ፤ አሸ​ነ​ፉ​ህም፤ በበ​ታ​ች​ህም አሽ​ክላ ዘረ​ጉ​ብህ፤ እነ​ር​ሱም ማስ​ተ​ዋል የላ​ቸ​ውም።


በዚያ ቀን ከኤ​ዶ​ም​ያስ ጥበ​በ​ኞ​ችን፥ ከዔ​ሳው ተራ​ራም ማስ​ተ​ዋ​ልን አጠ​ፋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብ​ሮ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም የዔ​ናቅ ዘሮች አኪ​ማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብ​ሮ​ንም በግ​ብፅ ካለ​ችው ከጣ​ኔ​ዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመ​ታት ተሠ​ርታ ነበር።


ሙሴም የግ​ብ​ፅን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በሚ​ና​ገ​ረ​ውና በሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ብርቱ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告