ኢሳይያስ 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ስለ ግብፅ የተነገረ ራእይ። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም የእጆቻቸው ሥራዎች በፊቱ ይዋረዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ስለ ግብጽ የተነገረ ንግር፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጻውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ስለ ግብጽ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል የሚከተለው ነው፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በደመና ሆኖ በፍጥነት ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጻውያን ጣዖቶች በፊቱ ይናወጣሉ፤ የግብጽ ሕዝብም በፍርሃት ይርበደበዳሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፥ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብፅም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል። 参见章节 |