ኢሳይያስ 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ኤፍሬም የሚጠጋበት ምሽግ አይኖርም፤ ከእንግዲህም ወዲያ ንጉሥ በደማስቆ አይነግሥም። የሶርያ ቅሬታ ሆይ፥ ከእስራኤል ልጆች ከክብራቸው የምትሻል አይደለህም” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣ የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤ የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ምሽግም ከኤፍሬም፥ መንግሥትም ከደማስቆ ይወገዳል፤ የሶርያም ትሩፍ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል፤ ይላል የሠራዊት ጌታ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እስራኤል ያለ መከላከያ ትቀራለች፤ ደማስቆም ነጻነትዋን ትገፈፋለች፤ ከጥፋት የተረፉ እነዚያ ሶርያውያን እንደ እስራኤል ሕዝብ የተዋረዱ ይሆናሉ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ምሽግም ከኤፍሬም፥ መንግሥትም ከደማስቆ ተወገደች የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节 |