Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እንደ ውኃ ለሞሉ፥ ከተ​ራራ በመ​ከ​ታ​ተል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ የውኃ ፈሳሽ ለሆ​ኑም ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ ወዮ​ላ​ቸው!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ወዮ! የብዙ ሕዝቦች የቍጣ ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል! አቤት፤ የሰዎች ከፍተኛ ጩኸት እንደ ኀይለኛ ውሃ ያስገመግማል!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እንደ ባሕር ሞገድ ለሚተም የብዙ ሕዝቦች ጩኸት፥ እንደ ኃያል የውኃ ሞገድ የሚያስገመግም ድምጽ ለሚያሰሙ ሕዝቦች ወዮላቸው!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እንደ ባሕር ሞገድ ድምፀ ለሚያሰሙ ለብዙ ወገን ስብስቦች ወዮላቸው! እንደ ኀይለኛ ጐርፍ ለሚጣደፉ ሕዝቦች ወዮላቸው!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እንደ ባሕር ሞገድ ድምፅ ለሚተምሙ ለወገኖች ብዛት፥ እንደ ኃይለኛም ውኃ ጩኸት ለሚጮኹ አሕዛብ ወዮላቸው!

参见章节 复制




ኢሳይያስ 17:12
21 交叉引用  

ቃላ​ቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገ​ራ​ቸ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።


አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ከሲ​ኦል አወ​ጣ​ሃት፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ለይ​ተህ አዳ​ን​ኸኝ።


አቤቱ፥ ነፍሴ አደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህን በመ​ው​ደድ ደስ አላት፤ ልቤም ሥጋ​ዬም በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አላ​ቸው።


በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተ​ሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሥ​ታ​ትና የአ​ሕ​ዛብ ድም​ፅም አለ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተዋ​ጊ​ዎች አሕ​ዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ።


ፍር​ዴን ለተ​ስፋ ይቅ​ር​ታ​ዬ​ንም ለት​ክ​ክ​ለኛ ሚዛን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በከ​ን​ቱና በሐ​ሰት የሚ​ታ​መኑ ከዐ​ውሎ ነፋስ አያ​መ​ል​ጡም።


በአ​ንቺ ላይ የተ​ሠራ መሣ​ሪያ ሁሉ እን​ዲ​ከ​ና​ወን አላ​ደ​ር​ግም፤ በአ​ንቺ ላይ ለፍ​ርድ የሚ​ነ​ሣ​ውን ድምፅ ሁሉ ታጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ጠላ​ቶ​ች​ሽም ሁሉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ርስት አላ​ቸው፤ ጻድ​ቃ​ኔም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሕ​ዛብ ሆይ፥ ዕወ​ቁና ደን​ግጡ፤ እስከ ምድር ዳር​ቻም ስሙ፤ ኀያ​ላን! ድል ሁኑ፤ ዳግ​መ​ኛም ብት​በ​ረቱ እንደ ገና ድል ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


በደም የተ​ለ​ወሰ ልብስ በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠል በቀር ለም​ንም አይ​ጠ​ቅ​ምም።


ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።


እነ​ሆም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር ከም​ሥ​ራቅ መን​ገድ መጣ፤ ድም​ፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተ​ምም ነበር፤ ከክ​ብ​ሩም የተ​ነሣ ምድር ታበራ ነበር።


አሁንም፦ ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።


ባረ​ፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስ​ራ​ኤል እልፍ አእ​ላ​ፋት ተመ​ለስ” ይል ነበር።


“በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ላይ ምል​ክት ይሆ​ናል፤ በም​ድር ላይም አሕ​ዛብ ይጨ​ነ​ቃሉ፤ ከባ​ሕ​ሩና ከሞ​ገዱ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ይሸ​በ​ራሉ።


ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤


አለኝም “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።


跟着我们:

广告


广告