Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት አሕ​ዛ​ብን ገር​ፎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ ከቍ​ጣ​ውም መቅ​ሠ​ፍት አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ው​ምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሕዝቦችን በማያቋርጥ ቍጣ የመታውን፣ ያለ ርኅራኄ እያሳደደ የቀጠቀጠውን ሰብሯል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሕዝቦችንም በማያቋርጥ ቁጣ የመታውን፥ ያለ ርኅራኄ ያለማቋረጥ ቀጥቅጦ አሕዛብን በማይበርድ ቁጣው የገዛውን ሰብሮአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነዚህ ገዢዎች በቊጣቸው ሕዝቦችን ሲጨቊኑ ኖረዋል፤ ያሸነፉአቸውንም ያለማቋረጥ ሲያሠቃዩአቸው ነበር፤

参见章节 复制




ኢሳይያስ 14:6
23 交叉引用  

ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔን ከመ​ቅ​ጣት አል​ተ​መ​ለ​ሰም፥ ከእ​ር​ሱም የተ​ነሣ ከሰ​ማይ በታች ያሉ አና​ብ​ርት ይዋ​ረ​ዳሉ።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች አና​ው​ጣ​ለሁ። በእ​ጄም ዓለ​ምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እንደ ተተወ እን​ቍ​ላ​ልም እወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ኔም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ የሚ​ቃ​ወ​መ​ኝም የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን ቀን​በ​ርና የአ​ለ​ቆ​ችን ቀን​በር ሰብ​ሮ​አ​ልና።


ለሚ​ያ​ዋ​ር​ዱ​አ​ችሁ ወዮ​ላ​ቸው! እና​ን​ተን ግን የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ችሁ የለም፤ የሚ​ወ​ነ​ጅ​ላ​ችሁ እና​ን​ተን የሚ​ወ​ነ​ጅል አይ​ደ​ለም፤ ወን​ጀ​ለ​ኞች ይጠ​መ​ዳሉ፤ ይያ​ዛ​ሉም፤ ብል እን​ደ​በ​ላው ልብ​ስም ያል​ቃሉ።


የቀ​ረ​ቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌ​ላው ጋር ያሉ የሰ​ሜን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ የዓ​ለም መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው፤ የሲ​ሳ​ርም ንጉሥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ይጠ​ጣል።


እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በዙ​ሪ​ያው ያላ​ችሁ ሁሉ ስሙ​ንም የም​ታ​ውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠን​ካ​ራ​ውም ሽመል፥ እን​ዴት ተሰ​በረ! ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሱ​ለት።


ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ! አን​ቺን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ፥ ቀንሽ ደር​ሶ​አ​ልና እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሣን። እኔ እን​ደ​ማ​ለ​ቅስ ሰም​ተ​ዋል፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናኝ የለም፤ ጠላ​ቶች ሁሉ መከ​ራ​ዬን ሰም​ተ​ዋል፤ አንተ አድ​ር​ገ​ኸ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ቃል ታመ​ጣ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም እንደ እኔ ይሆ​ናሉ።


ስለዚህ መረቡን ይጥላልን? አሕዛብንም ዘወትር ይገድል ዘንድ አይራራምን?


እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


跟着我们:

广告


广告