Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 14:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አሦ​ርን በም​ድሬ ላይ እሰ​ብ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በተ​ራ​ራ​ዬም ላይ እረ​ግ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ቀን​በ​ሩም ከእ​ነ​ርሱ ላይ ይነ​ሣል፤ ሸክ​ሙም ከጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይወ​ገ​ዳል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 አሦርን በምድሬ ላይ አደቅቃለሁ፤ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩ ከሕዝቤ ላይ ይነሣል፤ ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አሦርን በምድሬ ላይ እሰብራለሁ፥ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩም ከእነርሱ ላይ ይነሳል፥ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 አሦራውያንን ለእስራኤል በሰጠኋት ምድሬ ላይ እደመስሳቸዋለሁ፤ በተራሮቼም ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ ሕዝቤንም ከአሦራውያን የአገዛዝ ቀንበርና ከነበረባቸውም ከባድ ሸክም ነጻ አወጣቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አሦርን በምድሬ ላይ እሰብራለሁ፥ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፥ ቀንበሩም ከእነርሱ ላይ ይነሳል፥ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 14:25
19 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አ​ኩን ላከ፤ እር​ሱም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን አለ​ቆ​ቹ​ንም ከአ​ሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ። ወደ አም​ላ​ኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወ​ገቡ የወ​ጡት ልጆቹ በዚያ በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።


ስለ​ዚህ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ጌታ ሥራ​ውን ሁሉ በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ በፈ​ጸመ ጊዜ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐ​ይ​ኑ​ንም ከፍታ ትም​ክ​ሕት ይቀ​ጣል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን ቀን​በ​ርና የአ​ለ​ቆ​ችን ቀን​በር ሰብ​ሮ​አ​ልና።


ለሚ​ያ​ዋ​ር​ዱ​አ​ችሁ ወዮ​ላ​ቸው! እና​ን​ተን ግን የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ችሁ የለም፤ የሚ​ወ​ነ​ጅ​ላ​ችሁ እና​ን​ተን የሚ​ወ​ነ​ጅል አይ​ደ​ለም፤ ወን​ጀ​ለ​ኞች ይጠ​መ​ዳሉ፤ ይያ​ዛ​ሉም፤ ብል እን​ደ​በ​ላው ልብ​ስም ያል​ቃሉ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ።


በም​ድ​ያም ጊዜ እንደ ሆነ በላ​ያ​ቸው የነ​በ​ረው ቀን​በር ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና፥ በጫ​ን​ቃ​ቸው የነ​በ​ረ​ው​ንም፥ የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ንም በትር መል​ሶ​አ​ልና።


“አሦ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በዚያ ተገ​ደሉ፤ ሁሉም ድል ተነሡ፤ ወደ ጥልቅ ዐዘ​ቅ​ትም ጣሉ​አ​ቸው ሠራ​ዊ​ቱም በመ​ቃ​ብር ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ደሉ።


አን​ተና ጭፍ​ሮ​ችህ ሁሉ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉ ሕዝብ በም​ድረ በዳ ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለሚ​ና​ጠቁ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊ​ትም መብል አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ይህም ለሰላም ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።


የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ዳርቾቻችንንም በረገጠ ጊዜ እርሱ ይታደገናል።


አሁንም ቀንበሩን ከአንተ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ።


እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፣ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል።


跟着我们:

广告


广告