Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ ወደ ምድር ጥል​ቅም ትወ​ር​ዳ​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ነገር ግን ወደ ሲኦል፣ ወደ ጥልቁም ጕድጓድ ወርደሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን ወደ ሙታን ዓለም፥ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ወርደሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 14:15
13 交叉引用  

የሚ​መ​ለ​ከ​ቱ​ህም ይደ​ነ​ቃሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፦ በውኑ ምድ​ርን ያን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ያና​ወጠ፥


የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ሰዎች ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የሰ​ዎ​ችም ኵራት ትወ​ድ​ቃ​ለች፥ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤


በው​ኃው አጠ​ገብ ያሉ የዕ​ን​ጨ​ቶች ሁሉ ቁመት እን​ዳ​ይ​ረ​ዝም ራሱም ወደ ደመና እን​ዳ​ይ​ደ​ርስ ያንም ውኃ የሚ​ጠ​ጡት እን​ጨ​ቶች ሁሉ በር​ዝ​መ​ታ​ቸው ከእ​ርሱ ጋራ እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከሉ ሁሉም ወደ መቃ​ብር በሚ​ወ​ርዱ ሰዎች መካ​ከል በጥ​ልቅ ምድር ሞቱ።


ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣ​ል​ሁት ጊዜ ከመ​ው​ደቁ ድምፅ የተ​ነሣ አሕ​ዛ​ብን አን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥሁ፤ ውኃም የሚ​ጠጡ ሁሉ፥ ምር​ጦ​ችና መል​ካ​ሞች የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፥ የዔ​ድን ዛፎች ሁሉ በታ​ች​ኛው ምድር ውስጥ ተጽ​ና​ን​ተ​ዋል።


መቃ​ብ​ራ​ቸው በጕ​ድ​ጓዱ በው​ስ​ጠ​ኛው ክፍል ነው፤ ጉባ​ኤ​ዋም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል።


በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።


አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።


አን​ቺም ቅፍ​ር​ና​ሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወ​ር​ጃ​ለሽ።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


跟着我们:

广告


广告