Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተ​ሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሥ​ታ​ትና የአ​ሕ​ዛብ ድም​ፅም አለ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተዋ​ጊ​ዎች አሕ​ዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ በመንግሥታትም መካከል፣ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በተራሮች ላይ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ ይህም ጩኸት በአንድነት የተሰበሰቡ የብዙ ሕዝብ መንግሥታት ሁካታ ነው፤ የሠራዊት አምላክ ሠራዊቱን ለጦርነት እያዘጋጀ ነው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተከማቹት የአሕዛብ መንግሥታት የውካታ ጫጫታ አለ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊትን ለሰልፍ አሰልፎአል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 13:4
23 交叉引用  

እንደ ውኃ ለሞሉ፥ ከተ​ራራ በመ​ከ​ታ​ተል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ የውኃ ፈሳሽ ለሆ​ኑም ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ ወዮ​ላ​ቸው!


ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው ይሰ​ማሉ፤ ይህን ማን ነገ​ራ​ቸው? አን​ተን በመ​ው​ደድ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ዘር አስ​ወ​ግድ ዘንድ ፈቃ​ድ​ህን በባ​ቢ​ሎን ላይ አደ​ረ​ግሁ።


በሩቅ ላሉ አሕ​ዛ​ብም ምል​ክ​ትን ያቆ​ማል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ በፉ​ጨት ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ተ​ጣ​ደፉ ፈጥ​ነው ይመ​ጣሉ።


በዚ​ያም ቀን እንደ ባሕር መት​መም ይተ​ም​ሙ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወደ ምድ​ርም ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማን ያያሉ፤ ይጨ​ነ​ቃ​ሉም።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ በቅ​ጥ​ርም ውጭ የከ​በ​ቡ​አ​ች​ሁን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን የም​ት​ወ​ጉ​በ​ትን በእ​ጃ​ችሁ ያለ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም በዚ​ህች ከተማ መካ​ከል እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የሰ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ ታላቁ ሠራ​ዊቴ አን​በ​ጣና ደጎ​ብያ፥ ኩብ​ኩ​ባና ተምች ስለ በላ​ቸው ዓመ​ታት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በፍ​ርድ ሸለቆ ቀር​ቦ​አ​ልና ውካ​ታ​ዎች በፍ​ርድ ሸለቆ ተሰሙ።


ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


跟着我们:

广告


广告