Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 13:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ጐበ​ዞ​ችን ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም አይ​ም​ሩም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አይ​ራ​ሩም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ ሕፃናትን አይምሩም፤ ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ ሕፃናትን አይምሩም፤ ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በቀስታቸውና በፍላጻቸው ወጣቶችን ይገድላሉ፤ ሕፃናትን እንኳ አይምሩም፤ ለልጆችም ርኅራኄ የላቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይጨፈጭፋሉ፥ የማኅፀንንም ፍሬ አይምሩም፥ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 13:18
18 交叉引用  

አዛ​ሄ​ልም፥ “ጌታ​ዬን ምን ያስ​ለ​ቅ​ሰ​ዋል?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ክፋት ስለ​ማ​ውቅ ነው፤ ምሽ​ጎ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ይፍ ትገ​ድ​ላ​ለህ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትፈ​ጠ​ፍ​ጣ​ለህ፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ነ​ጥ​ቃ​ለህ፤” አለው።


ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።


ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ቸው ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ቤቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛሉ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያስ​ነ​ው​ራሉ።


አሁን ግን በአ​ንድ ቀን እነ​ዚህ ሁለት ነገ​ሮች በድ​ን​ገት ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ትና መበ​ለ​ት​ነት ስለ መተ​ቶ​ችሽ ብዛ​ትና ስለ አስ​ማ​ቶ​ችሽ ጽናት ፈጽ​መው ይመ​ጡ​ብ​ሻል።


ፍላ​ጾ​ቻ​ቸው ተስ​ለ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተለ​ጥ​ጠ​ዋል፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም መን​ኰ​ራ​ኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈ​ጠ​ራል።


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


ከን​ፈ​ራ​ቸ​ውም እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ ሁሉም ኀያ​ላን ናቸው።


ስለ​ዚህ ጐበ​ዛ​ዝቷ በአ​ደ​ባ​ባ​ይዋ ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በዚ​ያም ቀን ሰል​ፈ​ኞ​ችዋ ሁሉ ይጠ​ፋሉ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ቀስ​ትና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ይተ​ም​ማል፤ በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የባ​ቢ​ሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአ​ንቺ ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ።


በአ​ን​ቺም ወን​ድና ሴትን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ጐል​ማ​ሳ​ው​ንና ቆን​ጆ​ዪ​ቱን እበ​ት​ና​ለሁ፤


ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።


“እኔም ደግሞ በዐ​ይኔ አል​ራ​ራም፤ ይቅ​ር​ታም አላ​ደ​ር​ግም፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ” አለኝ።


የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፣ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፣ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ።


እርስዋ ግን ተማርካ ፈለሰች፣ ሕፃናቶችዋ በመንገድ ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፣ በከበርቴዎችዋም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።


跟着我们:

广告


广告