Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ባሕር ያደ​ር​ቃል፤ በኀ​ይ​ለ​ኛም ነፋስ እጁን በወ​ንዙ ላይ ያነ​ሣል፤ ሰባት ፈሳ​ሾ​ች​ንም ይመ​ታል፤ ሰዎ​ችም በጫ​ማ​ቸው እን​ዲ​ሻ​ገሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌታ በሚጋረፍም ነፋስ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔር የግብጽን ባሕረ ልሳን ያደርቃል፤ ማንም ሰው በእግሩ መሻገር እንዲችል የኤፍራጥስን ወንዝ በኀይለኛ ነፋስ መትቶ ወደ ትናንሽ ሰባት ጅረቶች ይከፋፍለዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እግዚአብሔርም የግብጽን ባሕር ያጠፋል፥ በትኩሱም ነፋስ እጁን በወንዙ ላይ ያነሣል፥ ሰባት ፈሳሾችንም አድርጎ ይመታዋል፥ ሰዎችም በጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 11:15
19 交叉引用  

ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ሄዱ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ወ​ር​ድ​ባ​ቸው ፍር​ሀ​ትና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ የተ​ነሣ ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ።


በባ​ሕር ውስጥ መን​ገ​ድን በኀ​ይ​ለ​ኛም ውኃ ውስጥ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያን ያደ​ረገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦


ቀላ​ይ​ዋ​ንም፥ “ደረቅ ሁኚ ፈሳ​ሾ​ች​ሽም ይድ​ረቁ” ይላል፤


እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አል​ነ​በ​ረም፤ ተጣ​ራሁ፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ እጄ ለማ​ዳን ጠን​ካራ አይ​ደ​ለ​ምን? ወይስ ለማ​ዳን አል​ች​ል​ምን? እነሆ፥ በገ​ሠ​ጽሁ ጊዜ ባሕ​ርን አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ውኃም በማ​ጣት ዐሣ​ዎ​ቻ​ቸው ይሞ​ታሉ፤ በጥ​ማ​ትም ያል​ቃሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቤ​ዣ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ወደ ጽዮ​ንም በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ክብር በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ደስ​ታ​ንና ተድ​ላን ያገ​ኛሉ፤ ኀዘ​ንና ልቅ​ሶም ይወ​ገ​ዳሉ።


በሙ​ሴም ቀኝ እጅ ውኃ​ውን ከፈ​ልሁ፤” ውኃ​ውም ተከ​ፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም አደ​ረ​ገ​ለት።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ንዙ ማዶ ባመ​ጣው ታላቅ ምላጭ በአ​ሦር ንጉሥ የራ​ሱ​ንና የእ​ግ​ሩን ጠጕር ይላ​ጨ​ዋል፤ ምላ​ጩም ጢሙን ደግሞ ይላ​ጫል።


ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ቱና ብዙ የሆ​ነ​ውን የወ​ንዝ ውኃ፥ የአ​ሦ​ርን ንጉ​ሥና ክብ​ሩን ሁሉ ያመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወን​ዙም ሞልቶ ይወ​ጣል፤ በዳ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤


ስለ​ዚህ፥ እነሆ በአ​ን​ተና በወ​ን​ዞ​ችህ ላይ ነኝ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ምድር ከሚ​ግ​ዶል ጀምሮ እስከ ሰዌ​ኔና እስከ ኢት​ዮ​ጵያ ዳርቻ ድረስ በጦ​ርና በቸ​ነ​ፈር ውድ​ማና ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።


ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም በክፉ ሰዎች እጅ እሰ​ጣ​ለሁ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንና ሞላ​ዋ​ንም በባ​ዕ​ዳን እጅ ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፣ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል።


ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


跟着我们:

广告


广告