Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 10:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የያ​ዕ​ቆ​ብም ቅሬታ በኀ​ያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የተረፉት ይመለሳሉ፣ ከያዕቆብ ቤት የተረፉት ወደ ኀያሉ አምላክ ይመለሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የተረፉት ይመለሳሉ፤ ከያዕቆብ ቤት የተረፉት እንኳን ሳይቀሩ ወደ ኀያሉ አምላክ ይመለሳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ከጥፋት የተረፉት ጥቂቶቹ ወደ ኀያል አምላካቸው በእውነት ይመለሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 10:21
17 交叉引用  

በስ​ደት በሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ ለቀ​ረው ሰው ሁሉ የሀ​ገሩ ሰዎች በብ​ርና በወ​ርቅ፥ በዕ​ቃም፥ በእ​ን​ስ​ሳም ይር​ዱት፤ ይህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሌላ ይሁን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፅን በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ታል፤ ይፈ​ው​ሳ​ታ​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለ​ሳሉ፤ እር​ሱም ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማል።


ያመ​ለ​ጠው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል።


እና​ንተ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ጀምሮ የተ​ሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትም ጀምሮ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ ስሙኝ።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


ከጽ​ዮን ታዳጊ ይመ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያር​ቃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢሳ​ይ​ያ​ስን አለው፥ “አን​ተና ልጅህ ያሱብ አካ​ዝን ትገ​ና​ኙት ዘንድ በል​ብስ አጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ወዳ​ለው ወደ ላይ​ኛው መታ​ጠ​ቢያ ቦታ ውጡ፤


ሕዝቡ ግን እስ​ከ​ተ​ቀ​ሠፉ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሱም፤ የሠ​ራ​ዊ​ት​ንም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ጉም።


ሕፃን ተወ​ል​ዶ​ል​ና​ልና፥ ወንድ ልጅም ተሰ​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ አለ​ቅ​ነ​ትም በጫ​ን​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አም​ላክ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም አባት፥ የሰ​ላም አለቃ ተብሎ ይጠ​ራል፤


በዚያ ወራት በዚ​ያም ዘመን፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ዚ​ህን በም​ድር የተ​ረ​ፉ​ትን ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእ​ስ​ራ​ኤል በደል ይፈ​ለ​ጋል፤ አይ​ኖ​ር​ምም፤ የይ​ሁ​ዳም ኀጢ​አት ይፈ​ለ​ጋል፥ ምንም አይ​ገ​ኝም።


ሰማ​ርያ በአ​ም​ላ​ክዋ ላይ ዐም​ፃ​ለ​ችና ፈጽማ ትጠ​ፋ​ለች፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።


በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ በማ​ለዳ ወደ እኔ ይገ​ሰ​ግ​ሳሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​መ​ለስ፤ እርሱ ሰብ​ሮ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይፈ​ው​ሰ​ናል፤ እርሱ መት​ቶ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይጠ​ግ​ነ​ናል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውር​ደ​ቱና ስድቡ በፊቱ ነው፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሱም፤ በዚ​ህም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ጉ​ትም።


ወደ ከንቱ ነገር ተመ​ለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስ​ትም ሆኑ፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከም​ላ​ሳ​ቸው ስን​ፍና የተ​ነሣ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ይህም በግ​ብፅ ምድር ውስጥ መሳ​ለ​ቂያ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል።


አስ​ቀ​ድሜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በደ​ማ​ስቆ ላሉት፥ ለይ​ሁዳ አው​ራ​ጃ​ዎ​ችም ሁሉ ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ንስሓ ገብ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለሱ ዘንድ፥ ለን​ስ​ሓ​ቸ​ውም የሚ​ገባ ሥራን ይሠሩ ዘንድ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告