ኢሳይያስ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ። በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፤ እንደ ተተወ እንቍላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ሰው እጁን ወደ ወፍ ጐጆ እንደሚሰድድ፣ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቍላል እንደሚሰበስቡ፣ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፤ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበስቡ፤ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የዓለም መንግሥታት ሁሉ በእኔ ፊት እንደ ወፍ ጎጆች ነበሩ፤ እንቊላል በቀላሉ እንደሚሰበሰብ ዐይነት ሀብታቸውን ሁሉ ሰብስቤ ወሰድኩ፤ ይህን ባደረግሁ ጊዜ የወፍ ላባ ያኽል እንኳ የተንቀሳቀሰ የለም፤ የወፍ ኩምቢ ያኽል እንኳ ድምፁን ያሰማ የለም።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እጄም የአሕዛብን ኃይል እንደ ወፍ ቤት አገኘች፥ የተተወም እንቍላል እንደሚሰበሰብ እንዲሁ እኔ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፥ ክንፉን የሚያራግብ አፉንም የሚከፍት የሚጮኽም የለም። 参见章节 |