Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 1:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እጄ​ንም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ አግ​ል​ሻ​ለሁ፤ ዝገ​ት​ሽ​ንም አነ​ጻ​ለሁ፤ ቆር​ቆ​ሮ​ሽ​ንም ሁሉ አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ዐመ​ፀ​ኞ​ችን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሕገ ወጦ​ች​ንም ከአ​ንቺ አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም አዋ​ር​ዳ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ ጕድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ ጉድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በከባድ ቊጣዬ እቀጣሻለሁ፤ ከዝገትሽ አጠራሻለሁ፤ ርኲሰትሽንም በማስወገድ አነጻሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፥ ዝገትሽንም በጣም አነጻለሁ፥ ቆርቆሮሽንም ሁሉ አወጣለሁ፥

参见章节 复制




ኢሳይያስ 1:25
18 交叉引用  

ወር​ቅ​ሽና ብርሽ ዛገ፥ የወ​ይን ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ሽም በወ​ይን ጠጅሽ ላይ ውኃን ይደ​ባ​ል​ቃሉ።


ስለ​ዚ​ህም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችና የፀ​ሐይ ምስ​ሎች ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ነሡ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ድን​ጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድን​ጋይ ባደ​ረገ ጊዜ ፥ እን​ዲሁ የያ​ዕ​ቆብ በደል ይሰ​ረ​ያል፤ ይህም ኀጢ​አ​ትን የማ​ስ​ወ​ገድ ፍሬ ሁሉ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴቶች ልጆ​ችና ወን​ዶች ልጆች እድፍ ያጥ​ባ​ልና፥ በፍ​ርድ መን​ፈ​ስና በሚ​ያ​ቃ​ጥል መን​ፈ​ስም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ደምን ያነ​ጻ​ልና።


ወና​ፉን የሚ​አ​ና​ፋው ደከመ፤ እር​ሳ​ሱም በእ​ሳት ቀለጠ፤ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውም መልሶ በከ​ንቱ ያቀ​ል​ጠ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።


አራ​ጣ​ንም በአ​ራጣ ላይ ይቀ​በ​ላሉ፤ ተን​ኰ​ልን በተ​ን​ኰል ላይ ይሠ​ራሉ፤ “እኔ​ንም ያው​ቁኝ ዘንድ እንቢ ብለ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀ​ል​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እፈ​ት​ና​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እን​ደ​ዚሁ አደ​ር​ጋ​ለ​ሁና።


ከእ​ና​ን​ተም ዘንድ ዐመ​ፀ​ኞ​ች​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን እለ​ያ​ለሁ፤ ከኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር ግን አይ​ገ​ቡም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሁላ​ችሁ አተላ ሆና​ች​ኋ​ልና ስለ​ዚህ እነሆ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።


እን​ዲ​ያ​ቀ​ል​ጡት እሳት ያና​ፉ​በት ዘንድ ብር​ንና መዳ​ብን፥ ብረ​ት​ንና እር​ሳ​ስን፥ ቆር​ቆ​ሮ​ንም በከ​ውር እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስቡ፥ እን​ዲሁ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ውስጥ እጨ​ም​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ አቀ​ል​ጣ​ች​ሁ​ማ​ለሁ።


ብርም በከ​ውር ውስጥ እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ በው​ስ​ጥዋ ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቴን እን​ዳ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም።


እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፣ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


ሰማ​ያት ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መላ​እ​ክት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። አሕ​ዛ​ብም ከሕ​ዝቡ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሁሉ እርሱ ጽኑዕ ነው ይላሉ፤ የል​ጆ​ቹን ደም ይበ​ቀ​ላ​ልና፥ ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥ ለሚ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ፍዳ​ቸ​ውን ይከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ዝ​ቡን ምድር ያነ​ጻል።”


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


跟着我们:

广告


广告