ሆሴዕ 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 የእስራኤልም ውርደቱና ስድቡ በፊቱ ነው፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፤ በዚህም ሁሉ እግዚአብሔርን አልፈለጉትም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እርሱንም አልፈለገም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የእስራኤልም ትዕቢት በራሱ ላይ መስክሮአል፤ ወደ አምላካቸው ወደ ጌታ ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የእስራኤል ሕዝብ ትምክሕታቸው በራሳቸው ላይ ይመሰክርባቸዋል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ ወደ አምላካቸው አልተመለሱም ከቶም አልፈለጉኝም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ መሰከረ፥ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም። 参见章节 |