Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኤፍ​ሬም በዘ​ለፋ ቀን ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች የታ​መ​ነ​ውን ነገር አሳ​የሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በቅጣት ቀን፣ ኤፍሬም ባድማ ይሆናል፣ በእስራኤል ነገዶች መካከል፣ በርግጥ የሚሆነውን ዐውጃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኤፍሬም በተግሣጽ ቀን ባድማ ይሆናል፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል እርግጥ የሆነውን ነገር አሳውቂያለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በቅጣት ቀን እስራኤል ባድማ ትሆናለች፤ ይህም በእርግጥ እኔ በእስራኤል ነገዶች ላይ እንዲደርስ የወሰንኩት ጥፋት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኤፍሬም በዘለፋ ቀን የፈረሰ ይሆናል፥ በእስራኤል ነገዶች ዘንድ በእርግጥ የሚሆነውን ነገር ገልጫለሁ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 5:9
23 交叉引用  

እነሆ፥ እርሱ ቢያ​ፈ​ርስ፥ ማን ይሠ​ራል? በሰ​ውም ላይ ቢዘ​ጋ​በት ማን ይከ​ፍ​ታል?


እነ​ር​ሱም፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ፥ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ ለመ​ው​ለ​ድም ኀይል የለም።


በመ​ጀ​መ​ሪያ መጨ​ረ​ሻ​ውን፥ ከጥ​ን​ትም ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ምክሬ ትጸ​ና​ለች፤ የመ​ከ​ር​ሁ​ት​ንም ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ እላ​ለሁ።


የቀ​ድ​ሞ​ውን ነገር ከጥ​ንት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ከአ​ፌም ወጥ​ቶ​አል፤ ድን​ገ​ትም ያደ​ረ​ግ​ሁት ምስ​ክር ሆኖ​አል፤ እር​ሱም ተፈ​ጽ​ሞ​አል።


ስለ​ዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድ​ር​ጎ​አል፤ የተ​ቀ​ረ​ጸው ምስ​ሌና ቀልጦ የተ​ሠ​ራው ምስ​ሌም ይህን አዘ​ዙኝ” እን​ዳ​ትል፥ የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ሆኑ በፊት ነገ​ር​ሁህ፤ አስ​ረ​ዳ​ሁ​ህም፤


ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት፥ መል​ካ​ሙን ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ፥ የፈ​ራ​ሃ​ቸው የሁ​ለቱ ነገ​ሥ​ታት ሀገር ባድማ ትሆ​ና​ለች።


እኔም ለኤ​ፍ​ሬም እንደ ብል፥ ለይ​ሁ​ዳም ቤት እንደ ነቀዝ እሆ​ን​በ​ታ​ለሁ።


እኔም ለኤ​ፍ​ሬም እንደ ነብር፥ ለይ​ሁ​ዳም ቤት እንደ አን​በሳ ደቦል እሆ​ና​ለ​ሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እወ​ስ​ድ​ማ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውም የለም።


ሲሄ​ዱም አሽ​ክ​ላ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎ​ችም አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መከ​ራ​ቸ​ውን ሲሰሙ እገ​ሥ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እስ​ራ​ኤል ተው​ጦ​አል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ዛሬ እንደ ግትቻ ዕቃ ሆኖ​አል።


የበ​ቀል ወራት መጥ​ቶ​አል፤ የፍ​ዳም ወራት ደር​ሶ​አል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ አበደ ነቢ​ይና ርኩስ መን​ፈስ እንደ አለ​በት ሰው ይታ​መ​ማል፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህና ከጠ​ላ​ት​ነ​ትህ ብዛት የተ​ነ​ሣም ቍጣ​ህን አበ​ዛህ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሚስ​ትህ በከ​ተ​ማ​ይቱ ውስጥ አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ር​ህም በገ​መድ ትከ​ፈ​ላ​ለች፤ አን​ተም በረ​ከ​ሰች ምድር ትሞ​ታ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከም​ድሩ ተማ​ርኮ ይሄ​ዳል።”


መሳ​ቂያ የሆኑ የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መቅ​ደ​ሶች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ቤት ላይ በሰ​ይፍ እነ​ሣ​ለሁ” አለ።


ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፥ ስለ ኃጢአትህም አፈረስሁህ።


ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።


ነገር ግን ጊዜው ሲደ​ርስ እኔ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። አስ​ቀ​ድሜ ግን ይህን አል​ነ​ገ​ር​ክ​ኋ​ች​ሁም ነበር፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ነበ​ር​ሁና።


跟着我们:

广告


广告