Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ፣ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ ቍስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እስራኤል መታመሙን፥ ይሁዳም መቊሰሉን ባየ ጊዜ፥ እስራኤል ወደ አሦር ፊቱን መለሰ፤ ርዳታም ለማግኘት ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ ነገር ግን እርሱ ሊያድናቸው ወይም ቊስላቸውን ሊፈውስ አልቻለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፥ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቍስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም።

参见章节 复制




ሆሴዕ 5:13
16 交叉引用  

በዘ​መ​ኑም የአ​ሶር ንጉሥ ፎሐ በም​ድ​ሪቱ ላይ ወጣ፤ ምና​ሔ​ምም የፎሐ እጅ ከእ​ርሱ ጋር እን​ዲ​ሆን አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ሰጠው።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


አካ​ዝም፥ “እኔ ባሪ​ያ​ህና ልጅህ ነኝ፤ መጥ​ተህ ከተ​ነ​ሡ​ብኝ ከሶ​ርያ ንጉ​ሥና ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እጅ አድ​ነኝ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


በዚያ ቀን ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “እኔ በቤቴ ውስጥ እን​ጀራ ወይም ልብስ የለ​ኝ​ምና ለሕ​ዝቡ አለቃ አል​ሆ​ንም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስብ​ራ​ትህ የማ​ይ​ፈ​ወስ፥ ቍስ​ል​ህም ክፉ ነው።


“ሐላም አመ​ነ​ዘ​ረ​ች​ብኝ፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


ለን​ጉሡ ለኢ​ያ​ሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስ​ረው ወደ አሦር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ ኤፍ​ሬ​ምን እፍ​ረት ይይ​ዘ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በም​ክሩ ያፍ​ራል።


ኤፍ​ሬም በሐ​ሰት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ይሁ​ዳም በተ​ን​ኰል ከበ​ቡኝ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐወ​ቃ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።


ከእ​ና​ንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለሱ። እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ኀጢ​አ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ግድ፤ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​በ​ለን፤ በወ​ይ​ፈ​ንም ፈንታ የከ​ን​ፈ​ራ​ች​ንን ፍሬ ለአ​ንተ እን​ሰ​ጣ​ለን።


ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም ትከ​ተ​ላ​ለች፤ ነገር ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤ ትፈ​ል​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለች፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከዛሬ ይልቅ የዚ​ያን ጊዜ ይሻ​ለኝ ነበ​ርና ተመ​ልሼ ወደ ቀደ​መው ባሌ እሄ​ዳ​ለሁ” ትላ​ለች።


ኤፍ​ሬ​ምም ልብ እን​ደ​ሌ​ላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብ​ፅን ጠሩ፤ ወደ አሦ​ርም ሄዱ።


ለብ​ቻ​ውም እን​ደ​ሚ​ቀ​መጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም እንደ ገና ለመ​ለመ፤ እጅ መን​ሻ​ንም ወደደ።


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


跟着我们:

广告


广告