ሆሴዕ 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሕዝቤም ከመኖሪያው ተነሥቶአል፤ እግዚአብሔርም በክብሩ ላይ ተቈጣ፤ ከፍ ከፍም አያደርገውም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤ ወደ ልዑል ቢጣሩም፣ በምንም ዐይነት አያከብራቸውም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ሕዝቤም ከእኔ ወደ ኋላ መመለስን በጽኑ ወደዱ፤ በአንድነትም ወደ ልዑሉ ይጣራሉ፥ እርሱ ግን ከፍ ከፍ አያደርጋቸውም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ሕዝቤ ከእኔ መራቅን ፈለጉ፤ ይሁን እንጂ ለእርዳታ ወደ ላይ ይጮኻሉ፤ ግን ማንም ከችግራቸው አያወጣቸውም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ሕዝቤም ከእኔ ይመለሱ ዘንድ ወደዱ፥ ወደ ላይም ቢጠሩአቸው ማንም ከፍ ከፍ ያደርጋቸው ዘንድ አይችልም። 参见章节 |