ሆሴዕ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የሰማርያ ሰዎች በቤትአዌን እንቦሳ አጠገብ ይኖራሉ፤ ሕዝቡ ያለቅሱለታል፤ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና እንዳዘኑበት እንዲሁ በክብሩ ደስ ይላቸዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣ በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ ሕዝቡም ያለቅስለታል፤ በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣ አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤ በምርኮ ከእነርሱ ተወስዷልና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የሰማርያ ሰዎች የቤትአዌንን እምቦሳ ፈሩ፤ ክብሩ ከእርሱ ተለይቶታልና ሕዝቡ ያለቅሱለታል፥ የጣዖቱ ካህናትም እሪ ብለው ይጮኹለታል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በሰማርያ ከተማ የሚኖሩ ሕዝቦች በቤትአዌን ስላለው በጥጃ ምስል በተሠራ ጣዖት በታላቅ ፍርሀት ይርበደበዳሉ፤ ክብሩ ስለ ተገፈፈ ሕዝቡ ያለቅሳሉ፤ የጣዖቱ ካህናትም እሪ ብለው ይጮኻሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የሰማርያ ሰዎች ስለ ቤትአዌን እምቦሳ ይፈራሉ፥ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና ሕዝቡ ያለቅሱለታል፥ የጣዖቱ ካህናትም በኀዘን ይንተባተባሉ። 参见章节 |