Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ክር​ስ​ቶስ ግን ለም​ት​መ​ጣ​ይቱ መል​ካም ነገር ሊቀ ካህ​ናት ሆኖ፥ የሰው እጅ ወደ አል​ሠ​ራት፥ በዚህ ዓለም ወደ አል​ሆ​ነ​ችው፥ ከፊ​ተ​ኛ​ዪቱ ወደ​ም​ት​በ​ል​ጠ​ውና ወደ​ም​ት​ሻ​ለው ድን​ኳን፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ክርስቶስ አሁን ስላሉት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ፣ በሰው እጅ ወዳልተሠራችው፣ ከዚህ ፍጥረት ወዳልሆነችው ታላቅና ፍጹም ድንኳን ገባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ነገር ግን ክርስቶስ እንደ ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ ስለሚሆነው መልካም ነገር፥ በምትበልጠውና በምትሻለው፥ በእጆችም ባልተሠራች፥ እርሷም ከፍጡራን ባልሆነች ድንኳን፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ነገር ግን ክርስቶስ በመምጣት ላይ ላሉት መልካም ነገሮች የካህናት አለቃ ሆኖ ተገልጦአል፤ እርሱ የገባባት ድንኳን ትልቅና ፍጹም ናት፤ ይህች ድንኳን በሰው እጅ ያልተሠራችና ከዚህ ፍጥረት ያልሆነች ናት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥

参见章节 复制




ዕብራውያን 9:11
30 交叉引用  

መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


ጠላ​ቶ​ቼም ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፥ በእኔ ላይም ክፋ​ትን ይመ​ክ​ራሉ።


ከጽ​ዮን ታዳጊ ይመ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያር​ቃል።


እኔ​ንም ከበ​ደ​ሉ​በት ኀጢ​አት ሁሉ አነ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም የበ​ደ​ሉ​ኝ​ንና ያመ​ፁ​ብ​ኝን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይቅር እላ​ለሁ።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” አለው።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


ሴቲ​ቱም፥ “ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲሕ እን​ደ​ሚ​መጣ እና​ው​ቃ​ለን፤ እር​ሱም በሚ​መጣ ጊዜ ሁሉን ይነ​ግ​ረ​ናል” አለ​ችው።


ነገር ግን ልዑል የሰው እጅ በሠ​ራው ቤት የሚ​ኖር አይ​ደ​ለም፤ ነቢይ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና።


የማ​ይ​ታ​የ​ውን እንጂ የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ አና​ደ​ር​ግም፤ የሚ​ታ​የው ኀላፊ ነውና፥ የማ​ይ​ታ​የው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ነው።


በም​ድር ያለው ማደ​ሪያ ቤታ​ችን ቢፈ​ር​ስም፥ በሰ​ማይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰው እጅ ያል​ሠ​ራው ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቤት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን።


የኀ​ጢ​አ​ትን ሰው​ነት ሸለ​ፈት በመ​ግ​ፈፍ በክ​ር​ስ​ቶስ መገ​ረዝ በሰው እጅ የአ​ል​ተ​ደ​ረገ መገ​ረ​ዝን በእ​ርሱ ሆና​ችሁ ተገ​ረ​ዛ​ችሁ።


ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እው​ነ​ተኛ አም​ሳል ሳይ​ሆን የነ​ገር ጥላ አለ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በየ​ዓ​መቱ ዘወ​ትር በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት በዚያ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊፈ​ጽም ከቶ አይ​ች​ልም።


አንድ ጊዜ ደግሞ ያለ​ውም ፍጡ​ራን ናቸ​ውና፥ የማ​ይ​ና​ወ​ጠው ይኖር ዘንድ፥ የሚ​ና​ወ​ጠ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ያሳ​ያል።


በዚህ የሚ​ኖር ከተማ ያለን አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​መ​ጣ​ውን እን​ሻ​ለን እንጂ።


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።


አሁ​ንም ከሰ​ማ​ያዊ ጥሪ ተካ​ፋ​ዮች የሆ​ና​ችሁ ቅዱ​ሳን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ንን ሐዋ​ር​ያና ሊቀ ካህ​ናት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ተመ​ል​ከቱ።


ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።


የሳ​ሌም ንጉሥ፥ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህን የሆነ፥ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብ​ር​ሃም ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሥቶ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ተገ​ና​ኝቶ ባረ​ከው።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።


跟着我们:

广告


广告