ዕብራውያን 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እንደ ተነገረም ዐሥራትን የሚቀበል ሌዊ ስንኳን በአብርሃም በኩል ዐሥራትን ሰጠ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እንዲያውም ዐሥራት የሚቀበለው ሌዊ፣ ራሱ በአብርሃም በኩል ዐሥራት ከፍሏል ማለት ይቻላል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በመሆኑም አሥራትን የሚቀበለው ሌዊ ራሱ እንኳን፥ በአብርሃም በኩል አሥራትን ሰጥቶአል፥ ማለት ያስችላል፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9-10 እንግዲህ መልከጼዴቅ አብርሃምን በተገናኘው ጊዜ ሌዊ ከአባቱ ከአብርሃም ገና ስላልተወለደ ዐሥራትን መቀበል የሚገባው ሌዊ ራሱ በአብርሃም አማካይነት ዐሥራትን ከፍሎአል ማለት ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤ 参见章节 |