Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከሌዊ ልጆ​ችም፥ ክህ​ነ​ትን የሚ​ቀ​በ​ሉት ከሕ​ዝቡ ማለት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እነ​ርሱ ምንም ከአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ቢወጡ ከእ​ነ​ርሱ ዐሥ​ራ​ትን በሕግ እን​ዲ​ያ​ስ​ወጡ ትእ​ዛዝ አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ክህነት የተሰጣቸው የሌዊ ልጆች ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም፣ ከሕዝቡ ማለት ከገዛ ወንድሞቻቸው ዐሥራት እንዲቀበሉ ሕጉ ያዝዛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከሌዊ ልጆችም፥ ክህነትን የሚቀበሉት ከሕዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነዚያ ክህነትን የሚቀበሉት የሌዊ ልጆች ከሕዝቡ ማለትም ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ፥ አሥራትን እንዲቀበሉ በሕግ ታዞላቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነዚያ በክህነት ሥራ ላይ የሚመደቡት የሌዊ ዘሮች ከሕዝቡ ከአብርሃም ዘር ማለትም ከወንድሞቻቸው ዐሥራት እንዲቀበሉ በሕግ ታዞላቸዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከሌዊ ልጆችም ክህነትን የሚቀበሉት ከህዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ፥ ከእነርሱ አሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትእዛዝ አላቸው፤

参见章节 复制




ዕብራውያን 7:5
15 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባ​ዛም፤ ሕዝ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ከአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከጕ​ል​በ​ትህ ይወ​ጣሉ።


ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት ሰዎች ሁሉ ከጕ​ል​በቱ የወ​ጡት፥ ከል​ጆቹ ሚስ​ቶች ሌላ፥ ሁላ​ቸው ስድሳ ሰባት ናቸው።


ነገር ግን ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል እንጂ ቤት የም​ት​ሠ​ራ​ልኝ አንተ አይ​ደ​ለ​ህም” አለው።


ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ፈን​ታ​ቸው እን​ዳ​ል​ተ​ሰጠ፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሌዋ​ው​ያ​ንና መዘ​ም​ራን እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ እር​ሻው እንደ ሄደ ተመ​ለ​ከ​ትሁ።


ዮሴ​ፍም አስ​ቀ​ድሞ በግ​ብፅ ነበረ። ከያ​ዕ​ቆብ ጕል​በት የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ ነፍ​ሶች ነበሩ፤


“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።


አን​ተም ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ እንደ መሠ​ዊ​ያ​ውና፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ እን​ዳ​ለው ሥር​ዐት ሁሉ ክህ​ነ​ታ​ች​ሁን ጠብቁ፤ የሀ​ብተ ክህ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ከሌ​ላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።”


“ዐሥ​ራት በም​ታ​ወ​ጣ​በት በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ሁሉ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ፥ ሁለ​ተኛ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ በከ​ተ​ሞ​ችህ ውስጥ ይበሉ ዘንድ፥ ይጠ​ግ​ቡም ዘንድ ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሃ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ስጣ​ቸው።


እንደ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ጠራ በቀር፥ ማንም ለራሱ ክብ​ርን የሚ​ወ​ስድ የለም።


መልከ ጼዴቅ በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ ገና በአ​ባቱ በአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ነበ​ርና።


跟着我们:

广告


广告