Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 7:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ኦሪ​ትስ የሚ​ሞት ሰውን ሊቀ ካህ​ናት አድ​ርጋ ትሾ​ማ​ለች፤ ከኦ​ሪት በኋላ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ሐላ ቃሉ ግን ዘለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ለ​ወጥ ፍጹም ወል​ድን ካህን አድ​ርጎ ሾመ​ልን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሕጉ ደካማ የሆኑትን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣው መሐላ ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾሟል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሕጉ ሰዎችን ድካም እያላቸው ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማል፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን፥ ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾመልን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሕግ የካህናት አለቆች አድርጎ የሚሾማቸው ደካሞች ሰዎችን ነው፤ ከሕግ በኋላ የመጣው የመሐላ ቃል ግን ለዘለዓለም ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ ሾሞአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።

参见章节 复制




ዕብራውያን 7:28
17 交叉引用  

ለጌ​ት​ነቱ መታ​ሰ​ቢ​ያን አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው።


የተ​ቀ​ባ​ውም ሊቀ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ላይ በደል እን​ዲ​ቈ​ጠ​ር​ባ​ቸው ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢ​አቱ ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​በ​ዋል።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱና ያችን ቀበሮ እን​ዲህ በሉ​አት፤ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋ​ን​ን​ትን አወ​ጣ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ት​ንም አድ​ላ​ለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሆም​ጣ​ጤ​ውን ቀምሶ፥ “ሁሉ ተፈ​ጸመ” አለ፤ ራሱ​ንም አዘ​ን​ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።


በኋላ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደ​ረ​ገው፥ ሁሉ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት በልጁ ነገ​ረን።


ብዙ ልጆ​ችን ወደ ክብር ሲያ​መጣ የመ​ዳ​ና​ቸ​ውን ራስ በመ​ከራ ይፈ​ጽም ዘንድ ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ሁሉ በእጁ ለተ​ያዘ፥ በእ​ር​ሱም ሁሉ ለሆነ ለእ​ርሱ ተገ​ብ​ቶ​ታ​ልና።


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።


አሁ​ንም ከሰ​ማ​ያዊ ጥሪ ተካ​ፋ​ዮች የሆ​ና​ችሁ ቅዱ​ሳን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ንን ሐዋ​ር​ያና ሊቀ ካህ​ናት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ተመ​ል​ከቱ።


ክር​ስ​ቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታ​መነ ነው፤ እኛም የም​ን​ደ​ፍ​ር​በ​ትን፥ የም​ን​መ​ካ​በ​ት​ንም ተስፋ እስከ መጨ​ረ​ሻው አጽ​ን​ተን ብን​ጠ​ብቅ ቤቱ ነን።


እን​ግ​ዲህ ወደ ሰማ​ያት የወጣ ታላቅ ሊቀ ካህ​ናት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አለን፤ በእ​ርሱ በማ​መን ጸን​ተን እን​ኑር።


እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም ሊቀ ካህ​ናት ይሆን ዘንድ ራሱን ያከ​በረ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ” ያለው እርሱ ራሱ ነው።


በመ​ሐላ የሾ​መ​ውን ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ፥ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም፤ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ” አለው።


እርሱ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ክህ​ነቱ አይ​ሻ​ር​ምና።


አባት የለ​ውም፤ እና​ትም የለ​ች​ውም፤ ትው​ል​ዱም አይ​ታ​ወ​ቅም፤ ለዘ​መኑ መጀ​መ​ሪያ፥ ለሕ​ይ​ወ​ቱም መጨ​ረሻ የለ​ውም፤ ክህ​ነቱ የወ​ልደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


跟着我们:

广告


广告