Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዛሬ የሚ​ባ​ለው ቀን ሳለ ከእ​ና​ንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢ​አት በሚ​ያ​ደ​ርስ ስሕ​ተት እን​ዳ​ይ​ጸና ሁል​ጊዜ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን መር​ምሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ነገር ግን ከመካከላችሁ ማንም በኀጢአት ተታልሎ ልቡ እንዳይደነድን፣ “ዛሬ” እየተባለ ሳለ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ነገር ግን ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ፥ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ፥ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይልቅስ ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ በየቀኑ ተመካከሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤

参见章节 复制




ዕብራውያን 3:13
13 交叉引用  

እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።


በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።


በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።


ኀጢ​አት በዚ​ያች ትእ​ዛዝ ምክ​ን​ያት አሳ​ተ​ችኝ፤ በእ​ር​ሷም ገደ​ለ​ችኝ።


የቀ​ድሞ ጠባ​ያ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ይህ​ንም ስሕ​ተት በሚ​ያ​መ​ጣው ምኞት ስለ​ሚ​ጠ​ፋው ስለ አሮ​ጌው ሰው​ነት እላ​ለሁ።


ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና እያጸናን እየመሰከርንላችሁም፥ አባት ለልጆቹ እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን ታውቃላችሁና።


ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።


ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።


ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የም​ክ​ርን ቃል እን​ድ​ት​ቀ​በሉ እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጥ​ቂት ቃል ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።


跟着我们:

广告


广告