ዕብራውያን 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በሥጋ የወለዱን አባቶቻችን የሚቀጡን፥ እኛም የምንፈራቸው ከሆነ፥ እንግዲያ ይልቁን ለመንፈስ አባታችን ልንታዘዝና ልንገዛ በሕይወትም ልንኖር እንዴት ይገባን ይሆን? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ከዚህም በተጨማሪ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ እንዴት በላቀ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር አይገባንም? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ከዚህም በቀር እኛ ሁላችን የሚቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ፥ በሕይወት ለመኖር ለመንፈሳዊ አባታችን በይበልጥ መታዘዝ እንዴት አይገባንም! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን? 参见章节 |