Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 12:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አንድ ጊዜ ደግሞ ያለ​ውም ፍጡ​ራን ናቸ​ውና፥ የማ​ይ​ና​ወ​ጠው ይኖር ዘንድ፥ የሚ​ና​ወ​ጠ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ያሳ​ያል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አንድ ጊዜ “ደግሜ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይናወጡት ጸንተው ይኖሩ ዘንድ፣ የሚናወጡት ይኸውም፣ የተፈጠሩት የሚወገዱ መሆናቸውን ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ዳሩ ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት ፍጡራን ነገሮች እንደሆኑና እንደሚለወጡ ያሳያል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ይህ “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይናወጡ ነገሮች ጸንተው እንዲኖሩ የሚናወጡ ወይም የተፈጠሩ ነገሮች መወገዳቸውን ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ዳሩ ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ የሚል ቃል የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት የተፈጠሩ እንደሚሆኑ ይለወጡ ዘንድ ያሳያል።

参见章节 复制




ዕብራውያን 12:27
19 交叉引用  

ሰማ​ያት እንደ መጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ይጠ​ቀ​ለ​ላሉ፤ ከወ​ይ​ንና ከበ​ለ​ስም ቅጠል እን​ደ​ሚ​ረ​ግፍ ከዋ​ክ​ብት ሁሉ ይረ​ግ​ፋሉ።


ተራ​ሮ​ችን እን​ዳ​ል​ቀ​ሥ​ፋ​ቸው እን​ዳ​ላ​ፈ​ል​ሳ​ቸ​ውም፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እን​ዳ​ይ​ነ​ዋ​ወጡ እንደ ማልሁ እን​ዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅ​ርታ አያ​ል​ቅም፤ የሰ​ላ​ምሽ ቃል ኪዳ​ንም አይ​ጠ​ፋም፤ መሓ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


“እነሆ፥ አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር ይሆ​ና​ልና፤ የቀ​ደ​ሙ​ትም አይ​ታ​ሰ​ቡም፤ ወደ ልብም አይ​ገ​ቡም።


“እኔ የም​ሠ​ራ​ቸው አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸን​ተው እን​ደ​ሚ​ኖሩ፥ እን​ዲሁ ዘራ​ች​ሁና ስማ​ችሁ ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ፍርድ ያለው እስ​ኪ​መጣ ድረስ ይህች ደግሞ አት​ሆ​ንም፤ ለእ​ር​ሱም እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤


ለይሁዳ አለቃ ለዘሩባቤል ተናገር እንዲህም በል፦ ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ፣


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


የዓ​ለም ተስ​ፋው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ መም​ጣት ይጠ​ባ​በቅ ነበ​ርና።


ነገር ግን አስቶ በባ​ር​ነት ከሚ​ገ​ዛው ከዚህ ወጥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ አገ​ኙ​አት የነ​ጻ​ነት ክብር ይገባ ዘንድ ተስፋ አለው።


የበሉ እን​ዳ​ል​በሉ ይሆ​ናሉ፤ የጠ​ጡም እን​ዳ​ል​ጠጡ ይሆ​ናሉ፤ የዚህ ዓለም ተድላ ሁሉ ያል​ፋ​ልና።


ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ አንተ አስ​ቀ​ድሞ ምድ​ርን መሠ​ረ​ትህ፤ ሰማ​ያ​ትም የእ​ጆ​ችህ ሥራ ናቸው።


በዚህ የሚ​ኖር ከተማ ያለን አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​መ​ጣ​ውን እን​ሻ​ለን እንጂ።


ክር​ስ​ቶስ ግን ለም​ት​መ​ጣ​ይቱ መል​ካም ነገር ሊቀ ካህ​ናት ሆኖ፥ የሰው እጅ ወደ አል​ሠ​ራት፥ በዚህ ዓለም ወደ አል​ሆ​ነ​ችው፥ ከፊ​ተ​ኛ​ዪቱ ወደ​ም​ት​በ​ል​ጠ​ውና ወደ​ም​ት​ሻ​ለው ድን​ኳን፥


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፤ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደ ፊት የለም።


እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ሐዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዐት አልፎአልና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። ለእኔም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።


跟着我们:

广告


广告