Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ካህን ሁሉ በየዕለቱ ቆሞ አገልግሎቱን ያከናውናል፤ ኀጢአትን ማስወገድ ከቶ የማይችሉትን እነዚያኑ መሥዋዕቶች ዘወትር ያቀርባል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሊቀ ካህናትም ሁሉ በየዕለቱ እያገለገለ እነዚያን ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን መሥዋዕቶች ደጋግሞ ለማቅረብ ይቆማል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እያንዳንዱ ካህን ኃጢአትን ማስወገድ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ዘወትር እያቀረበ በየቀኑ ቆሞ ያገለግላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤

参见章节 复制




ዕብራውያን 10:11
21 交叉引用  

ዕለት ዕለ​ትም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረይ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም ባደ​ረ​ግህ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ቅዱ​ስም ይሆን ዘንድ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ።


“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ብዛት ለእኔ ምን​ድን ነው?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን የአ​ውራ በግ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የፍ​ሪ​ዳን ስብ ጠግ​ቤ​አ​ለሁ፤ የበ​ሬና የአ​ውራ ፍየ​ልም ደም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።


ከም​ድ​ርም የተ​ቀ​ደሰ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ለሚ​ቀ​ርቡ ለመ​ቅ​ደሱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለካ​ህ​ናቱ ይሆ​ናል፤ ለቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ሆን ስፍራ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም የሚ​ሆን የተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይሆ​ናል።


ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን?


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ቀን በየ​ዕ​ለቱ እን​ዲሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ይህ ነው፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ዕለት ዕለት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


በወሩ መባቻ ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን እንደ ሕጋ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።


ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እው​ነ​ተኛ አም​ሳል ሳይ​ሆን የነ​ገር ጥላ አለ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በየ​ዓ​መቱ ዘወ​ትር በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት በዚያ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊፈ​ጽም ከቶ አይ​ች​ልም።


የላ​ምና የፍ​የል ደም ኀጢ​አ​ትን ሊያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አይ​ች​ል​ምና።


ሊቀ ካህ​ናት ሁሉ ስለ ኀጢ​አት መባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ ከሰው ተመ​ርጦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾ​ማ​ልና።


እር​ሱም እንደ እነ​ዚያ ሊቃነ ካህ​ናት አስ​ቀ​ድሞ ስለ ራሱ ኀጢ​አት በኋ​ላም ስለ ሕዝቡ ኀጢ​አት ዕለት ዕለት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ራሱን ባቀ​ረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።


እር​ሱም የመ​ቅ​ደ​ስና የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ድን​ኳን አገ​ል​ጋይ ነው፤ እር​ስ​ዋም በሰው ሳይ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ተ​ከ​ለች ናት።


በም​ድር ቢሆን ኖሮ፥ ሊቀ ካህ​ናት ባል​ሆ​ነም ነበር፤ በኦ​ሪት ሕግ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርቡ ካህ​ናት በእ​ር​ስዋ አሉና።


跟着我们:

广告


广告