ሐጌ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ባሪያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፥ በዚያ ቀን እወስድሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እኔ መርጬሃለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንደ ቀለበት ማተሚያ አደርግሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዚያ ቀን ባሪያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፤ እኔ እወስድሃለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘እንደ ማተሚያ ቀለበቴ አደርግሃለሁ፤ እኔ መርጬሃለሁና’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በዚያ ቀን ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ባርያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፥ እወስድሃለሁ፥ ይላል ጌታ፥ እንደ ማተሚያ ቀለበት አደርግሃለሁ፥ እኔ መርጬሃለሁና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 አገልጋዬ ዘሩባቤል ሆይ! እኔ አንተን መርጬሃለሁ፤ አንድ ቀን መሪ እንድትሆን አንተን ለይቼ እንደ ማኅተም ቀለበቴ አደርግሃለሁ፤” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ባሪያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፥ በዚያ ቀን እወስድሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔ መርጬሃለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንደ ቀለበት ማተሚያ አደርግሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节 |