Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በም​ድር ላይ ሥጋ ያለው የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ ወፉም፥ እን​ስ​ሳ​ውም፥ አራ​ዊ​ቱም፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሹ​ም​ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በምድር ላይ የነበሩ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፦ ወፎች፣ የቤት እንሰሳት፣ የዱር እንስሳት በምድር የሚርመሰመሱ ፍጥረታት፣ ሰዎችም በሙሉ ጠፉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ወፎችና እንስሶች፥ አራዊት፥ ሰዎችም ሁሉ ሞቱ። በምድር ላይ ያሉት ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ጠፉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ወፎችና እንስሶች፥ አራዊት፥ ሰዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ሞቱ። በምድር ላይ ያሉት ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ጠፉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቃሹም ሁሉ ሰውም ሁሉ ጠፉ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 7:21
20 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ድር አራ​ዊ​ትን እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ በም​ድር የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ እን​ደ​የ​ወ​ገኑ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደር​ሶ​አል፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ምድር በግፍ ተመ​ል​ታ​ለ​ችና፤ እኔም እነሆ፥ ከም​ድር ጋር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እኔም እነሆ፥ ከሰ​ማይ በታች የሕ​ይ​ወት ነፍስ ያለ​ውን ሥጋ ሁሉ ለማ​ጥ​ፋት በም​ድር ላይ የጥ​ፋት ውኃን አመ​ጣ​ለሁ፤ በም​ድር ያለው ሁሉ ይጠ​ፋል።


ከሰ​ባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ዝናብ አዘ​ን​ባ​ለ​ሁና፤ የፈ​ጠ​ር​ሁ​ት​ንም ፍጥ​ረት ሁሉ ከም​ድር ሁሉ ላይ አጠ​ፋ​ለ​ሁና።”


ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይሞ​ታል፥ ሟችም ሁሉ ወደ ተፈ​ጠ​ረ​በት መሬት ይመ​ለ​ሳል።


ምድር ደነ​ገ​ጠች፤ ታወ​ከ​ችም፤ ምድር ጐሰ​ቈ​ለች፤ ተነ​ዋ​ወ​ጠ​ችም።


ስለ​ዚህ ምድር ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ በእ​ር​ስዋ የተ​ቀ​መጡ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ በም​ድር የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ይቸ​ገ​ራሉ፤ ጥቂት ሰዎ​ችም ይቀ​ራሉ።


ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ።


እሳት በፊ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ለች፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ል​ባል ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ሪቱ በፊ​ታ​ቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእ​ር​ሱም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


የጥፋት ውሃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።


ኖኅ ወደ መር​ከብ እስከ ገባ​በት ቀን ድረስ ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ሲያ​ገ​ቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥ​ፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድ​ርጎ አጠፋ።


ዓለም ባለ​ማ​ወቅ ለከ​ንቱ ነገር ተገ​ዝ​ቶ​አ​ልና በተ​ስፋ ስለ አስ​ገ​ዛው ነው እንጂ በፈ​ቃዱ አይ​ደ​ለም።


እስ​ካ​ሁን ዓለም ሁሉ ያዘ​ነና የተ​ከዘ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።


ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥


跟着我们:

广告


广告