Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 50:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች አባ​ታ​ቸው እንደ ሞተ በአዩ ጊዜ እን​ዲህ አሉ፥ “ምና​ል​ባት ዮሴፍ ያደ​ረ​ግ​ን​በ​ትን ክፋት ያስ​ብ​ብን ይሆ​ናል፤ ባደ​ረ​ግ​ን​በ​ትም ክፋት ሁሉ ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ብን ይሆ​ናል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ ቢበቀለን ምን እናደርጋለን?” ተባባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ “ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፥ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸው ከሞተ በኋላ “ዮሴፍ ባደረስንበት በደል ሁሉ እስከ አሁንም ቂም ይዞ ሊበቀለን ቢፈልግ ምን እናደርጋለን?” ተባባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዪ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ ምናልባትም ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል ባደረግንበትን ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 50:15
13 交叉引用  

እነ​ር​ሱም ወደ እነ​ርሱ ሳይ​ቀ​ርብ ከሩቅ አስ​ቀ​ድ​መው አዩት፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ በእ​ርሱ ላይ ተማ​ከሩ።


እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።


ሦስት ቀን ያህ​ልም በግ​ዞት ቤት ጨመ​ራ​ቸው።


ዮሴ​ፍና ወን​ድ​ሞቹ፥ አባ​ቱ​ንም ሊቀ​ብሩ ከእ​ርሱ ጋር የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ አባ​ቱን ከቀ​በረ በኋላ ወደ ግብፅ ተመ​ለሱ።


ወደ ዮሴ​ፍም መጡ፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አባ​ትህ ገና ሳይ​ሞት እን​ዲህ ብሎ አዝ​ዟል፦


ገን​ዘ​ቡን በአ​ራጣ የማ​ያ​በ​ድር፥ በን​ጹሑ ላይ መማ​ለ​ጃን የማ​ይ​ቀ​በል። እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ርግ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ወ​ክም።


ክፋ​ትን ወደ ጠላ​ቶች ይመ​ል​ሳ​ታል፤ በእ​ው​ነ​ት​ህም አጥ​ፋ​ቸው።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤


በል​ባ​ቸው የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕግ ሥራ ያሳ​ያሉ፤ ከሥ​ራ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ይታ​ወ​ቃል፤ ሕሊ​ና​ቸ​ውም ይመ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ልም።


跟着我们:

广告


广告