ዘፍጥረት 47:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፥ “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፤ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለምና፤ ራብም በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፤ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንቀመጥ።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፥ ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፥ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለም፥ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።” አሉት ፈርዖንን። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በከነዓን ምድር ራብ እጅግ ከመበርታቱ የተነሣ ለእንስሶቻችን ግጦሽ ስላጣን ለጊዜው በዚህች አገር ለመኖር መጥተናል፤ ስለዚህ አገልጋዮችህ በጌሴም ምድር እንድንኖር ፍቀድልን።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን። 参见章节 |