Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 47:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ብሩም በግ​ብፅ ምድ​ርና በከ​ነ​ዓን ምድር አለቀ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ እን​ዲህ ሲሉ፥ “በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት እህል ስጠን፤ ብሩ አል​ቆ​ብ​ና​ልና።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የግብጽና የከነዓን ሕዝቦችም ገንዘባቸው ባለቀ ጊዜ፣ ግብጻውያን ሁሉ ወደ ዮሴፍ ቀርበው፣ “የምንበላው እህል ስጠን፤ ገንዘባችን ዐልቆብናል፤ ዐይንህ እያየ እንዴት በራብ እንለቅ?” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በግብጽ ምድርና በከነዓን ምድር ብሩም በሸመታ አለቀ፥ የግብጽ ሰዎች ሁሉም ወደ ዮሴፍ እየመጡ፦ “የምንመገበው ስጠን፥ ስለምን በፊትህ እንሞታለን? ብሩ አልቆብናልና” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በዚህ ሁኔታ የግብጽና የከነዓን ሕዝቦች ገንዘባቸውን በእህል ሸመታ ስለ ጨረሱ፥ ግብጻውያን ወደ ዮሴፍ ተሰብስበው መጥተው “የምንመገበው እህል ስጠን! ገንዘባችንን ስለ ጨረስን በራብ ማለቃችን ነው!” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ብሩም በግብፅ ምድርን በከነዓን ምድር አለቀ፤ የግብፅ ሰዎችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ እንዲህ ሲሉ፦ እንጀራ ስጠን ስለ ምን በፊትህ እንሞታለን? ብሩ አልቆብናልና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 47:15
11 交叉引用  

በግ​ብፅ ምድር ስለ​ሚ​ሆ​ነው ስለ ሰባቱ ዓመ​ታት ራብ እህሉ ለሀ​ገሩ ሁሉ ተጠ​ብቆ ይኑር፥ ምድ​ሪ​ቱም በራብ አት​ጠ​ፋም።”


ዮሴ​ፍም፥ “ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ብር ከአ​ለ​ቀ​ባ​ችሁ በከ​ብ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈንታ እህል እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ” አለ።


በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


እርሱ ከፍ ባለ በጽ​ኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖ​ራል፤ እን​ጀ​ራም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ውኃ​ውም የታ​መ​ነች ትሆ​ና​ለች።


የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤


የሱ​ኮ​ት​ንም ሰዎች፥ “ተር​በ​ዋ​ልና እኔን ለተ​ከ​ተሉ ሰዎች እባ​ካ​ችሁ እህል ስጡ​አ​ቸው፤ እኔም የም​ድ​ያ​ምን ነገ​ሥ​ታት ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን አሳ​ድ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።


ከዚ​ያም ወደ ፋኑ​ሄል ወጣ፤ ለፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች እን​ዲሁ አላ​ቸው፤ የፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች የሱ​ኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለ​ሱ​ለት።


አሁ​ንም አም​ስት እን​ጀራ በእ​ጅህ ካለ፥ ወይም በእ​ጅህ ያለ​ውን ስጠኝ” አለው።


ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ግ​ሩ​ሃል፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ በመ​ል​ካም ቀን መጥ​ተ​ና​ልና ብላ​ቴ​ኖች በፊ​ትህ ሞገስ ያግኙ፤ በእ​ጅ​ህም ከተ​ገ​ኘው ለል​ጅህ ለዳ​ዊት እባ​ክህ፥ ላክ።”


跟着我们:

广告


广告