Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 46:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በግ ጠባቂ ሁሉ ለግ​ብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም እን​ድ​ት​ቀ​መጡ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ታ​ችን ጀም​ረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም እን​ስሳ አር​ቢ​ዎች ነን” በሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እናንተ፣ ‘እኛ ባሮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከዚያም ግብጻውያን ከብት አርቢዎችን እንደ ጸያፍ ስለሚቈጥሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ‘እኛ ልክ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የምንተዳደረው በግ በማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። በግ አርቢዎች በግብጻውያን ዘንድ የተናቁ ስለ ሆኑ ይህን በመናገር በጌሴም ምድር ለመኖር ፈቃድ ታገኛላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ትቀመጡ እንዲህ በሉት፦ እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስለ አሁን ድረስ እኝም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 46:34
17 交叉引用  

በአ​ብ​ራ​ምና በሎጥ መን​ጎች ጠባ​ቆች መካ​ከ​ልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና ፌር​ዛ​ው​ያን በዚ​ያች ምድር ተቀ​ም​ጠው ነበር።


አብ​ራ​ምም ሎጥን አለው፥ “እኛ ወን​ድ​ማ​ማች ነንና በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በእ​ረ​ኞ​ቼና በእ​ረ​ኞ​ችህ መካ​ከል ጠብ አይ​ሁን።


የጌ​ራራ እረ​ኞች ከይ​ስ​ሐቅ እረ​ኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚ​ያ​ች​ንም ጕድ​ጓድ ስም “ዐዘ​ቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነ​ርሱ በድ​ለ​ው​ታ​ልና።


በዚ​ያም ቀን ከተ​ባ​ቶቹ ፍየ​ሎች ሽመ​ል​መሌ መሳ​ይና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከእ​ን​ስ​ቶቹ ፍየ​ሎች ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ነጭ ያለ​በ​ትን ማን​ኛ​ው​ንም ሁሉ፥ ከበ​ጎ​ቹም መካ​ከል ጥቁ​ሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለል​ጆቹ ሰጣ​ቸው።


ያዕ​ቆ​ብም ልጁን ዲናን የኤ​ሞር ልጅ እን​ዳ​ስ​ነ​ወ​ራት ሰማ፤ ልጆ​ቹም ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በም​ድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕ​ቆ​ብም ልጆቹ እስ​ኪ​መጡ ድረስ ዝም አለ።


ወን​ድ​ሞ​ቹም በሴ​ኬም የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን በጎች ይጠ​ብቁ ዘንድ ሄዱ።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆ​ነው ጊዜ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር የአ​ባ​ቱን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ሚስ​ቶች ከባ​ላና ከዘ​ለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላ​ቴና ነበረ፤ ዮሴ​ፍም የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውን ወሬ ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ እስ​ራ​ኤል ያመጣ ነበር።


ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና።


በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም ምድ​ርም ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ወደ እኔም ትቀ​ር​ባ​ለህ። አን​ተና ልጆ​ችህ የል​ጆ​ች​ህም ልጆች፥ በጎ​ች​ህና ላሞ​ችህ፥ የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ፥


አባ​ታ​ች​ሁ​ንና ንብ​ረ​ታ​ች​ሁን ሁሉ ይዛ​ችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ምድር በረ​ከት ሁሉ እሰ​ጣ​ች​ሁ​አ​ለሁ፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ድልብ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


እነ​ር​ሱም ከብት ጠባ​ቂ​ዎች፥ መንጋ አር​ቢ​ዎች ናቸው፤ በጎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ላሞ​ቻ​ቸ​ውን፥ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አመጡ።


ዮሴ​ፍም አባ​ቱ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አኖረ፤ ፈር​ዖን እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸ​ውም በግ​ብፅ ምድር በተ​ሻ​ለ​ችው በራ​ምሴ ምድር ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።


ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድ​ሞች፥ “ሥራ​ችሁ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈር​ዖ​ንን፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፥ አባ​ታ​ች​ንም ከብት ጠባ​ቂ​ዎች ነን” አሉት።


ፈር​ዖ​ን​ንም እን​ዲህ አሉት፥ “በም​ድር ልን​ቀ​መጥ በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጣን፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጎች የሚ​ሰ​ማ​ሩ​በት ስፍራ የለ​ምና፤ ራብም በከ​ነ​ዓን ምድር እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌ​ሤም ምድር እን​ቀ​መጥ።”


በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።”


በዚ​ያም ቀን የም​ድር ሁሉ አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የውሻ ዝንብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝቤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትን የጌ​ሤ​ምን ምድር እለ​ያ​ለሁ።


ሙሴም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እን​ሠ​ዋ​ለ​ንና እን​ዲሁ ይሆን ዘንድ አይ​ቻ​ልም፤ እነሆ፥ ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እኛ በፊ​ታ​ቸው ብን​ሠዋ በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​ናል።


跟着我们:

广告


广告