ዘፍጥረት 45:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እግዚአብሔርም በምድር ላይ እንድትድኑና እንድትተርፉ እመግባችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ነገር ግን እግዚአብሔር ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግና ዘራችሁ ከምድር ላይ እንዳይጠፋ በማሰብ ከእናንተ አስቀድሞ ወደዚህ ላከኝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እግዚአብሔር አስቀድሞ ወደዚህ የላከኝ በዚህ በአስደናቂ ዘዴ የእናንተን ሕይወት በማዳን በምድር ላይ ዘር እንዲቀርላችሁ አስቦ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ። 参见章节 |