Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 43:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ዮሴ​ፍም ታወከ፤ አን​ጀቱ ወን​ድ​ሙን ናፍ​ቆ​ታ​ልና፤ ሊያ​ለ​ቅ​ስም ወደደ፤ ወደ እል​ፍ​ኙም ገብቶ በዚያ አለ​ቀሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለ ተነካ፣ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰወር ያለ ቦታም ፈልጎ፣ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለ ተነካ፥ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰወር ያለ ቦታም ፈልጎ፥ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ ስለ ተነካ ከዚያ ተነሥቶ ሄደ፤ ወደ እልፍኙም ገብቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ዮሴፍም ቸኮለ፥ አንጀቱ ወንድሙን ናፍቆታልና ሊያለቅስም ወደደ ወደ እልፍኙም ገብቶ ከዚያ አለቀሰ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 43:30
16 交叉引用  

ዮሴ​ፍም ከእ​ነ​ርሱ ዘወር ብሎ አለ​ቀሰ፤ ደግ​ሞም ወደ እነ​ርሱ ተመ​ልሶ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ስም​ዖ​ን​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለይቶ ወስዶ በፊ​ታ​ቸው አሰ​ረው።


ቃሉ​ንም ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሰሙ፤ በፈ​ር​ዖን ቤትም ተሰማ።


ዮሴ​ፍም ሰረ​ገ​ላ​ውን አዘ​ጋጀ፤ አባ​ቱ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ሊገ​ና​ኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአ​የ​ውም ጊዜ አን​ገ​ቱን አቀ​ፈው፤ ረዥም ጊዜም አለ​ቀሰ።


ደኅ​ነ​ኛ​ውም ሕፃን የነ​በ​ራት ሴት አን​ጀ​ትዋ ስለ ልጅዋ ታው​ኳ​ልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይ​ደ​ለም፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ለእ​ር​ስዋ ስጣት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት” ብላ ለን​ጉሡ ተና​ገ​ረች። ያች​ኛ​ዪቱ ግን፥ “አካ​ፍ​ሉን እንጂ ለእ​ኔም ለእ​ር​ስ​ዋም አይ​ሁን” አለች።


በእ​ው​ነት ኤፍ​ሬም ለእኔ የተ​ወ​ደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም ሕፃን ነው፤ በእ​ርሱ ላይ በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር አስ​በ​ዋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ አን​ጀቴ ታወ​ከ​ች​ለት፤ ርኅ​ራ​ኄም እራ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኔም “አም​ል​ኮ​ቴን ትተ​ሃል አልሁ፤ ኤፍ​ሬም ሆይ! እን​ዴት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ዴ​ትስ እደ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ? እን​ዴ​ትስ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በው​ስጤ ተና​ው​ጣ​ለች፤ ምሕ​ረ​ቴም ተገ​ል​ጣ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ገ​ለ​ገ​ልሁ በፍ​ጹም መከ​ራና በል​ቅሶ ከአ​ይ​ሁ​ድም ሴራ የተ​ነሣ በደ​ረ​ሰ​ብኝ ፈተና እየ​ተ​ጋ​ደ​ልሁ፥


ስለ​ዚ​ህም ትጉ፤ እኔ ሁላ​ች​ሁ​ንም ሳስ​ተ​ምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም ቀንም እን​ባዬ እን​ዳ​ል​ተ​ገታ ዐስቡ።


ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት።


በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ደስታ፥ ወይም በፍ​ቅር የልብ መጽ​ና​ናት፥ ወይም የመ​ን​ፈስ አን​ድ​ነት፥ ወይም ማዘ​ንና መራ​ራ​ትም በእ​ና​ንተ ዘንድ ካለ፦


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መረ​ጣ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንና ወዳ​ጆች፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ርኅ​ራ​ኄን፥ ቸር​ነ​ት​ንና ትሕ​ት​ናን፥ የው​ሀ​ት​ንና ትዕ​ግ​ሥ​ትን ልበ​ሱት።


እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ።


ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?


跟着我们:

广告


广告