Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 43:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ባሪ​ያህ ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችን ደኅና ነው፤ ገና በሕ​ይ​ወት አለ።” ዮሴ​ፍም አለ፥ “ሰው​የው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ከው ነው።” ራሳ​ቸ​ው​ንም ዝቅ አድ​ር​ገው ሰገ​ዱ​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እነርሱም መልሰው፣ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው በአክብሮት እጅ ነሡት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እነርሱም መልሰው፥ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው በአክብሮት እጅ ነሡት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እነርሱም “አገልጋይህ አባታችን በሕይወት አለ፤ ጤንነቱም የተሟላ ነው” አሉት። ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እነርሱ አሉት፦ ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው ገና በሕወይት አለ፤ አጎንብሰውም ሰገዱለት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 43:28
8 交叉引用  

እነሆ፥ እኛ በእ​ርሻ መካ​ከል ነዶ ስና​ስር ነበ​ርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእ​ና​ን​ተም ነዶ​ዎች በዙ​ርያ ከብ​በው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”


ዮሴ​ፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእ​ጃ​ቸው ያለ​ውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው ሰገ​ዱ​ለት።


በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰ​ፈር ከሳ​ኦል ወገን አንድ ሰው ልብ​ሱን ቀድዶ፥ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊ​ትም በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።


እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።


ቤር​ሳ​ቤ​ህም አጎ​ን​ብሳ ለን​ጉሡ ሰገ​ደች፤ ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።


ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም ከሞተ በኋላ የይ​ሁዳ አለ​ቆች ገብ​ተው ለን​ጉሡ ሰገዱ፤ ንጉ​ሡም ሰማ​ቸው።


ሙሴም አማ​ቱን ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመ​ውም፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ሰላ​ምታ ተሰ​ጣጡ፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ገቡ።


跟着我们:

广告


广告