Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 41:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ዮሴ​ፍም እንደ ተና​ገረ ሰባቱ የራብ ዓመት መም​ጣት ጀመረ። በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብጽ ምድር ግን ምግብ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፥ በመላው የግብጽ ምድር ግን ምግብ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው፥ ሰባቱ የራብ ዓመቶች መግባት ጀመሩ፤ በሌሎች አገሮች ሁሉ ራብ ሆነ፤ ይሁን እንጂ በመላው የግብጽ ምድር በቂ ምግብ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 ዮሴፍም እንደ ተናገረ የሰባቱ ዓመት ራብ ጀመረ። በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ በግብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 41:54
13 交叉引用  

ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው።


ደግ​ሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመ​ጣል፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የነ​በ​ረ​ው​ንም ጥጋብ ሁሉ ይረ​ሱ​ታል፤ ራብም ምድ​ርን ሁሉ ያጠ​ፋል፤


በግ​ብፅ ምድር የነ​በ​ረ​ውም ሰባቱ የጥ​ጋብ ዓመት አለፈ፤


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግ​ብፅ እን​ዳለ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ወደ​ዚያ ውረዱ፤ እን​ድ​ን​ድ​ንና በራብ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ከዚያ ሸም​ቱ​ልን።”


ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና።


በዚ​ያም አን​ተና የቤ​ትህ ሰዎች የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ እን​ዳ​ት​ቸ​ገሩ እመ​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አም​ስት ዓመት ቀር​ቶ​አ​ልና፤


በም​ድ​ርም ሁሉ እህል አል​ነ​በ​ረም፤ ራብ እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ ከራ​ብም የተ​ነሣ የግ​ብፅ ምድ​ርና የከ​ነ​ዓን ምድር ተጐዳ።


ኤል​ሳ​ዕም ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላ​ትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ፤ በም​ታ​ገ​ኚ​ውም ስፍራ ተቀ​መጪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ራብን ጠር​ቶ​አ​ልና፤ ሰባት ዓመ​ትም በም​ድር ላይ ይቆ​ያል” ብሎ ተና​ገ​ራት።


ሙሴ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ደ​ሰ​ውን አሮ​ን​ንም በሰ​ፈር አስ​ቈ​ጧ​ቸው።


በግ​ብ​ፅና በከ​ነ​ዓን ሀገር ሁሉ ረኃ​ብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሚ​በ​ሉት አጡ።


跟着我们:

广告


广告