Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 40:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈር​ዖን ራስ​ህን ይቈ​ር​ጥ​ሃል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ ይሰ​ቅ​ል​ሃል፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም ሥጋ​ህን ይበ​ሉ​ታል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ፈርዖን ከዚህ እስር ቤት አውጥቶ ራስህን ካስቈረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ያሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ በእንጨትም ላይ ይስቅልሃል ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 40:19
17 交叉引用  

እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈር​ዖን ሹመ​ት​ህን ያስ​ባል፤ ወደ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃ​ነ​ት​ህም ይመ​ል​ስ​ሃል፤ ጠጅ አሳ​ላፊ በነ​በ​ር​ህ​በት ጊዜ ስታ​ደ​ር​ገው እንደ ነበ​ረው እንደ ቀድ​ሞው ሹመ​ት​ህም የፈ​ር​ዖ​ንን ጽዋ በእጁ ትሰ​ጣ​ለህ።


በላ​ይ​ኛ​ውም መሶብ ፈር​ዖን የሚ​በ​ላው ጋጋ​ሪው በያ​ይ​ነቱ የሠ​ራው መብል ነበ​ረ​በት፤ ወፎ​ችም በራሴ ላይ ከመ​ሶቡ ይበሉ ነበር።”


ዮሴ​ፍም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “የሕ​ል​ምህ ትር​ጓ​ሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈር​ዖን የተ​ወ​ለ​ደ​በት ዕለት ነበር፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ ግብር አደ​ረገ፤ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹን አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹን አለቃ በአ​ሽ​ከ​ሮቹ መካ​ከል ዐሰበ።


የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ በዕ​ን​ጨት ላይ ሰቀ​ለው፤ ዮሴፍ እንደ ተረ​ጐ​መ​ላ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እንደ ተረ​ጐ​መ​ልን እን​ደ​ዚ​ያው ሆነ፤ እኔ ወደ ሹመቴ ተመ​ለ​ስሁ፤ እር​ሱም ተሰ​ቀለ።”


የኢ​ዮ​ሔል ልጅ ሩጻ​ፋም ማቅ ወስዳ ከመ​ከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰ​ማይ እስ​ኪ​ዘ​ንብ ድረስ በድ​ን​ጋይ ላይ ዘረ​ጋ​ችው፤ በቀ​ንም የሰ​ማይ ወፎች፥ በሌ​ሊ​ትም የዱር አራ​ዊት ያር​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወ​ችም።


ከል​ጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠ​ንና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ረ​ጠው በሳ​ኦል ሀገር በገ​ባ​ዖን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠ​ቅ​ላ​ቸ​ዋ​ለን።” ንጉ​ሡም፥ “እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ” አለ።


አን​ተና ጭፍ​ሮ​ችህ ሁሉ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉ ሕዝብ በም​ድረ በዳ ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለሚ​ና​ጠቁ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊ​ትም መብል አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ሁሉ የሰ​ወ​ር​ኋ​ች​ሁና ያል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የለም።


እኛ​ንስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እኛ የኦ​ሪ​ትን መር​ገም በመ​ሸ​ከሙ ከኦ​ሪት መር​ገም ዋጅ​ቶ​ናል፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”


ከዚ​ህም በኋላ መት​ተው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ በአ​ም​ስ​ቱም ዛፎች ላይ ሰቀ​ሉ​አ​ቸው፤ እስከ ማታም ደረስ በዛ​ፎቹ ላይ ተሰ​ቅ​ለው ቈዩ።


የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋ​ህ​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ አን​ተን በእጄ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ እመ​ታ​ህ​ማ​ለሁ፤ ራስ​ህ​ንም ከአ​ንተ እቈ​ር​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ህ​ንና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሬሶች ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት ዛሬ እሰ​ጣ​ለሁ። ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር እን​ዳለ ያው​ቃሉ፤


跟着我们:

广告


广告